Discussion Forum

 ኢትዮጲያዊነት ስፈተን::

ኢትዮጲያዊነት ስፈተን

ኢትዮጲያዊነት ማለት በአገሪቷ በኢትዮጲያ ውስጥ ተወልደህ ማደግ ብቻ ሳይሆን፣ ከኢትዮጲያ ውጪም ተወልደህ አደገህ ሆነ ወይም በተሰቦችህ ትውልደ ኢትዮጲያዊ ከሆኑ፣ ኢትዮጲያዊ ዜጋ የማይኮንበት ምንም አይነት ምክንያት የለም። አልፎ ተርፎም፣ ሌላ ውጫዊ ዜጋ ሆነህም ሳለ የኢትዮጲያ ዜግነት እፈልጋለሁ ብለህ አመልክተህ፣ ማመልከቻህ ተቀባይነትን አግኝቶ ከሆነ፣ ዜጋ የማትሆንበት ምክንያት ፈጽም የለም።ባለንበት በውጪው ዓለም በተለይም በካናዳ ውስጥ የሌለ አንድም ጎሣና ዘር የለም። ነገር ግን ይህ ሁሉ ዘር በአንድ ላይ ተሳስሮ ከሕግ በታች ከመሆንም አልፎ፣ ሁሉ ራሱን የሚያስጠራ የራሱ የሆነ ማህበር አቋቋሞ በእኩልነት ይስተናገዳል። እያንዳንዱም ድንበር ዘለል በሆነ መልኩ ባህሉን፣ ወጉን፣ አመጋገቡን፣ አለባበሱንና ለሎችንም በመጋራት፤ በቋንቋው ልዩነት ይሁን በዘር ልዩነት ምንም አይነት ተፅዕኖ ሳያስከትልና በአገሪቱም እኮኖሚ ላይ ዕድገትን እንጂ ውድቀትን በማያመጣና በማያሻማ ሁኔታ አብሮ ተሳስሮ ተጋብቶና ተዋልዶ ይኖራል።

ይህንን አቦል እንበልና ወደበረካው (እኛው ጋ) ስንሄድ፣ ይህ ሁሉ ካናዳዊ ዜጋ ፖለቲካዊ አመለካከት ስላለው የፈለገውንም ፖርቲ መርጦ ይተዳደራል። በኛ አገር ወይም እኛ የኢትዮጲያዊ ዜጋ የሆንን ሁሉ በነ መንገድ መሄድ አለብህ አለበለዚያ ተቃዋሚን እንደአንጃ አድርገን በማየት፣ ከመከራከር ከመወያየት ይልቅ አተካራ፣ ግልምጫ፣ እኔ ያልኩት ካልተፈጸመ በስተቀር፤ እንኳንና አንድ ሰው፣ድፍን ዘጠና ሚሊየን ሰው ብናገር ደንታ የማይሰጠን በርካታዎች ነን።

ትናንት ኢትዮጲያ ብዙ የምሬት ኑሮ አሳልፋለች። ሻዕቢያ አገራችንን ለመገንጠል፣ የትግራይ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ራሱን ከነበረው ዘውዳዊ ጨቋኝ አገዛዝ ነጻ ለማውጣት ሲል በደረገው አመጽ፣ በርካታ ድልድዮች፣ በርካታ የልማት አውታሮች፣ ከሁሉም በላይ ውድ የሆነው ብዙ የሰው ልጅ ሕይወት አልፎአል። አገራችን ከነበረችበት ከ2% እድገቷ በግምት ወደ 00.01% አሽቆልቁላ ነበር። ቀጣይነት ያልነበረው የፖለቲካ ሥርዓት ከአውሮፖና ከሩቅ ምሥራቅ አገራት ያከተመው በ17ኛው ም ዓ ነበር። ታዲያ የኛ እድገትስ በዚያው ደርጃ መለካት አለበት ወይስ እንደአይሲሲ ደግሞ ራቅ ወዳለው ወደድንጋይ ዘመን (stone age) የባሰውን ማሽቆልቆል አለበት?

“በአገራችን የስልጣን ምንጬ ከምርጫ ኮሮጆ እንደሆነ ህገ-መንግሥታችን ላይ በግልጽ ተደንግጓል። ይሁንና ሰማያዊ ፓርቲ ሁለት አማራጭን በአንዴ ለመጠቀም የሚያስብ ይመስላል። እነዚህ ሁለት አማራጮች አንደኛው በህጋዊ መንገድ ሲሆን ሌላኛው ድግሞ የአቋራጭ መንገድ ነች።
አማራጭ አንድ በህጋዊ መንገድ በምርጫ በማሸነፍ የሚደረግ ሲሆን፤ ይህ አመቺ ሳይሆን ሲቀር ደግሞ አማራጭ ሁለት የቀለም አብዮት መንገድ የሆነችው 
የሃሰት ውንጀላን በማራገብ ወደ ነውጥ መጓዝ ነው።

ሰማያዊ ፓርቲ ነገሮችን በአግባብ ያለመረዳት እንጂ ከሁከትና ብጥብጥ የሚተርፈን ነገር ሥርዓት አልበኝነት፣ ሞት፣ ስደት የኢኮኖሚ ድቀት፣ እንግልት፣ መበታተን፣ በመጨረሻም ለዓለም አቀፍ አሸባሪዎች የተመቸ መደላድል መፍጠር እንደሆነ ሊያውቁት ይገባል። በሰላማዊ መንገድ እታገላለሁ የሚሉ ፓርቲዎች ሁሉ ለአገሪቱ ህጎች ተገዥ የመሆን ግዴታ ይኖርባቸዋል። በተለይ ሰማያዊ ፓርቲ ይህችን ነገር ደግሞ ደጋግሞ ሊያስብባት ይገባል።
ሰማያዊ ፓርቲ ከወዲሁ አባላቶቼ፣ ደጋፊዎቼ፣ ወዘተ በገዥው ፓርቲ ካድሬዎችና የፀጥታ ሰራተኞች ወከባ ደርሶባቸዋል፣ ተደብድበዋል፣ ታስረዋል፣ ወዘተ የሚሉ ወሬዎችን እያሰራጩ የሚገኙት ከፈጸሙት ወንጀልሳቢያ ከህግ ተጠያቂነት ለማምለጥ ይመስላል። 
ምርጫ በውጤቱ ሊለካ አይችልም። ማንም አሸነፈ ማንም የምርጫው ሂደት ዴሞክራሲያዊና አሳታፊ እስከነበረ ድረስ ውጤቱን የመቀበል ግዴታ ይኖርብናል። የቀለም አብዮተኞች እነርሱ ካላሸነፉ በስተቀር ምርጫው ዴሞክራሲያዊ ነው የሚል እምነት የላቸውም። ከአዲስ አበባ የኢሀደግ ወጣቶች ሊግ” መልዕክት የተወሰደ

ዛሬ ኢትዮጲያዊነታችን በጥያቄ ውስጥ ገብቶ ላሌን ለደካማ አመለካከቶቻችን (ዘረኝነት፣ ጎጠኝነት፣ ጥላቻ፣ መከፋፈል፣ ራስ ወዳድነት፣ እኔው ነኝ ላንተ የማውቀው በማለትና ወዘተ…) ተገዢ በመሆን በሌላው ላይ ጣት እየጠቆምን ነገር ግን እጅግ በጣም የባሰብን ሆነን እንገኛለን። የሚደረገው አፍራሽ ድርጊት ጤናማውን የአገሪቱን ሕዝብ አልፎ በውጪ አገር ተወላጆች ዘንድ ከመድረሱም ሌላ አስበሳ ለአገራችን የሚያበረክተውን ሕዝብ ሁሉ በክለናል። ታዲያ ማንን ነው ሕዝባችን ብለን መጥራት የምንችለው? ጉሮሮውን ዘግተን ሕዝቡ ተበሳጭቶ አመጽ እንዲያነሳ ቢደረግም ምን ያህል ሰው ነው በዚህ አመጽ ላይ ተሳታፊ የሚሆነውና የሆነው? በጩሔት የሚመጣ መንግሥት ለአሣር ነው። ከግብፅ፣ ሊቢያ፣ ቱኒሲያ፣ የመን፣ ሶሪያንና ወዘተ… አግሮች መማር በቂ ነው።

ታዲያ መበቀል ከተፈለገ ሕዝቡን አይደለም። ምን አይነት አዕምሮ ቢኖረን ነው ልማታችን ላይ ለማመፅ የምንሞክረው? ቢሞከርስ የት ያደርሳል? አንቺም ዘሮ ዜሮ፣ እኔም ዜሮ ዜሮ፣ ሁላችንም ዜሮ ስለመሆን መተንበይ አያሻም።

የሕዝባችንን ሰቆቃ ለንግድ እና ለፖለቲካ መጠቀሚያ ማድረግ ነገ ማንንም ከታሪክ ተጠያቂነት ነጻ የሚያደርገን አይደለም። ሕዝብ በዘሩ በቀየውና በቋንቋው ራሱን ችሎ ማስተዳደር አግባብ ካልሆነ፣ ለምን እዚህ አገር ያለውን መንግሥት ትክክል አይደላችሁም አንልም? ማንም ይዝለል፣ ይውጣ፣ ይውረድ፣ ይጩህ፤ ኢትዮጲያ ከሚትጓዝበት መንገድ ሊመልሳት የሚችል አንድም መንግሥት ሆነ ሃይል ለዘለዓለም አይኖርም። በርግጥ መስተካከል የሚገቡ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ፣ እነዚህም በሂደት በውይይት እንጂ በጉልበት አይደለም። ትግራይ አንድ መንግሥት፣ አፋር አንድ መንግሥት፣ ሶማሌ አንድ መንግሥት፣ ኦሮሞ አንድ መንግሥት፣ ደቡቡ አንድ መንግሥት፣ አማራ አንድ መንግሥት፣ በንሻንጉል አንድ መንግሥትና ጋምቤላ አንድ መንግሥት፤ ታዲያ በማን አገር የማን መንግሥት መጥቶ ነው ሊገዛን የሚችለው? ከአሁን ወዲያ ዲፕሎማሲ ብቻ ነው የምሰራው። አበቃ!!!!

     Give your opinion.