Discussion Forum

 ዝሙትና ሴሰኝነት ምህረት የለሌው ወንጀል ነው።

ዝሙትና ሴሰኝነት በውጪው አለም እጅግ በጣም አስጸያፊ ከሚባሉ ከሰው መግደል ወንጀል ባላነሰ እንዲያውም በተመጣጠነ መልኩ የሚያስቀጣ ወንጀል ከመሆኑም ሌላ በተለይ የመንግሥት ባለሥልጣን ከሆንክ ወዲያውኑ ራስህን በራስህ ከስራው ካባረርክ በኋላ ወደ ፍርድ ትቀርባለህ። በኛ አገር የሰው ሚስት ደፍሮ፣ የሰው ትዳር አፍርሶ፣ ትዳሩ የፈረሰበትን የትዳሩን ባለበት በወህኒ በማስገባት ሲቀጡ ሕዝቡ ነገሩን እንደነውር እንጂ እንደወንጀል ሳይቆጥር ብዙ ጊዜ አሳልፎታል። ቀደም ሲል በደርግ ጊዜ በስልጣን ላይ የነበሩ የደርግ ካድሬዎችና ባለስልጣናት ለአቅሜ ሄዋን ያልደርሱትን ሕጻናት ከመድፈራቸውም ሌላ እናቶቻቸውንም ጭምር በስልጣናቸው ተደግፈው መጫወቻ አድርገው የማለፋቸው ጉዳይ እየጸጸተን እያለ፣ ዛሬ ደግሞ ታሪክ እንደገና በሌላ ቋንቋና መልክ መጥቶ ሕዝባችንን ለውርደት ከማብቃቱም አልፎ ሴቶቻችን ብቻ ሳይሆን እኛው ራሳችን እንደሴት ልጆቻችን መደፈራችን ምን ያህል አስቀያሚ ውርደት መሆኑ ነው? እነዚህ በስልጣን ላይ ያሉትን ለኛ ይሰራሉ በሚል እምነት ጥለን ሁላችንም ደፋ ቀና ብለን ብናስመርጥም፣ እነርሱ ግን ለሆዳቸው ማደራቸውን በግልጽ አሳይተውናል። ታዲያ የኛዎቹን የራሳችንን የድሮ የባልባት ልጆችና ልጅ ልጆች ነፍጠኛ ናቸው ብለን የሚንሳደበው እንዚህን ገና ስልጣንን ለኪሳቸው ማዳበሪያ የሚሮጡትን ለመሾም ነው? ከነዚህስ እነዚያ አይሻሉም? እንዲያውም ባህላዊ ግርማና ሞገስ የተላበሱ የኛዎቹ ሆነው አንድነታችንን የማያፈርሱ ይሆኑ ነበር። ምስኪን የቁጫውን ሕዝብ፣ የጎፋውን፣ ሕዝብ፣ የጋሞውን ሕዝብ ለማሰረ በማስፈራራት የሚፈልጉትን ለማድረግ ወደኋላ እንደማይሉና ምን ያህል እንደናቁን በግልጽ አሳይተውናል። ልማት ልማት ብለው የሚያወሩት ልማት፣ አንድ የመኪና መንገድ ከወላይታ እስከአርባምንጭ ለመስራት ሰባት አመት ማጥፋት ነው ልማት? ደርግ ገቢ ሳይኖረው አዞ እርባታን መስርቶ አልፎአል። አሁን ከለም በቂ ዕርዳት በሚገኝበት ወቅት ያንን ቦታውን በማሻሻል፣ ጀልባዎችና ሌሎችም ነገሮች በማመቻቸት እንደአርባምጭነቷ ለአለም ማሳየት ያልቻለው ልማት ነው ልማት? ነጭ ሳር ፓርክ ይባል እንጂ እዚያ ለመድረስ ምንም ምቹ መንገድ የሌለበት ፓርክ ነው ፓርክ ማለት? ከአርባ ምንጭ በላይ ምንጭ ያለባት አርባምንጭ ውሃ የምትጠማበት ልማት ነው ልማት ማለት? ሰሜን በአማራው ክልል ለውጣቸው በአሃዝ የተደገፈ (በፕላን የተያዘው 5.5ቢሊየን ሆኖ ሰኬቱ ደግም 5.9 ቢሊየን) ሆኖ እናገኛለን። ታዲያ ደቡብ ውስጥ መንግሥት በጀት መድቦ አያውቅም ማለት ነው? በጀት ከተመደበስ ለሕዝብ በየጊዜው መገለጽ የለበትም? እንዲያው እንደዚህ አይነት ነገር እየተሞከረ ነው የሚል የተስፋ ንግግርና ጉራ መች ይሆን የሚቆመው? መላውን ኢትዮጲያ ባጠቃላይ ስናስተያይ በደቡብ ውስጥ መንግሥት አለ ለማለት በፍጹም አያስደፍርም። ምክንያቱም መዋቅር የተባሉት ሁሉም እንደየአገባባቸው ተደራጅተው ከትልቅ ቆዳ በተሠራ ምቹ ወንበርና በጣም ከሰለጠነ ከኦፍስ ጠረጰዛ ጋር ሽክ ብሎ እናያለን። ፍሬውስ የት ነው? ት/ቤቶች፣ መንገዶች፣ የውሃ ጉድጓዶች፣ ፓርኮች፣ ጤና ጣቢያዎች ኦና ሆነው ልውጥ እየተመኙና በሌላው እየቀኑ ይታያሉ። ታዲያ የት ነው ያለው በደቡብ ውስጥ 10.1 እድገት የተመዘገበው? ማዶላንና ማዶላዎችን በማውጠንጠን ሕዝባችን ለመበታተን የሚትጥሩት ሕዝብ ማገልገላችሁ ነው? አልፎ ተርፎም በፖሊስና በፈድራል ፖሊስ ገና ቂጣ ያልጠገበውን ሚስኪን ህዝብ የምታሳድዱት? የአፋር ክልል፣ የሶማሌ ክልል፣ የበንሻንጉል ክልልና የጋምቤላ ክልል በለውጥና በምርት ደረጃ ከኛ በጣም የራቁና ወደኋላ የቀሩ ነበሩ። ዛሬ በምግብ ራሳቸውን ወደሚችሉበት ደረጃ ደርሰዋል። የትግራይ፣ የአማራ፣ የኦሮሞ፣ የአደሬና የአዲስ አበባ ክልልማ በተክኖሎጂ ጭምር መጥቆአል። ታዲያ እኛ ያለውነው በተመሳሳይ ኢትዮጲያ ነው ወይስ ሌላ? አሃዝ የሌለው የተለመደ ሪፖርት ኪሳራ እንጂ እድገት አይደለም። ለም መሬት አለን፣ ብዙ፣ ብዙ ነገሮች፣ ታዲያ የት አለ ውጤቱ? በአሃዝ ግለጹልን። ደቡብ አያሳዝንም። ሌላው ጥገኛ እያሉ ያን የመሰለ ምርጥ የጀግኖች አገር በራሳችው በሙሰኞችና በጥገኞች ሲሰደብ? ጋሞ ጎፋ ውስጥ ያለህ እያንዳንድህ ጉቦንና ጉበኞችን በማሳደግ ለዚህ ያበቃሄው አንተው ራስህ ነህ፣ አንተ ብታጋልጣቸውና ለህግ ብታቀርባቸው ኖሮ ይህ ሁሉ አይከሰትም ነበር። አሁን የእቅዱ አዲስ ጅምር ነውና፣ በአይን በማይታይ፣ ባልተጨበጠ፣ በአሃዝ ባልተደገፈ፣ ሕልም ማመን ይቅርብህ። የተመደበልህን በጀት ውጪውንና ገቢውን አሳውቁ በሏቸው። አለዚያ ግን ለንግድ እንደቀረበ ዕቃ ይነግዱብሃል። መጠንቀቅ ከአሁን ጀምሮ ነው። ዝሙትና ሴሰኝነት በህብረተሰብህ ውስጥ በመረጥካቸው ሰዎች ሲፈጠር እያየህ ዝም ማለቱ አሁንም አንተው ነህ ደካማ፣ አሁኑኑ ማቆም ትችላለህ። ይበቃል ማለት መቻል አለብን። ቸር ይግጠመን። መልካም አዲስ አመት።

     Give your opinion.