Discussion Forum

 በ18 ሚሊዮን የህዝብ ገንዘብ ለአንድ ባለስልጣን የአስፓልት መንገድ ተነጠፈለት::

በ18 ሚሊዮን የህዝብ ገንዘብ ለአንድ ባለስልጣን የአስፓልት መንገድ ተነጠፈለት

ውድ የዚህ ጽሑፍ አንባቢዎች 
አሁን የሚነግራቹ ነገር ተረት ተረት አልያም በግለሰብ ጥላቻ ምክንያት የሚነዛ የፈጠራ ወሬ አይደልም፡፡ ይልቁንም በሴነ ወር 2007 ዓ/ም በማን አለብኝነትና ደረቅ ድፍረት የተፈጸም እጅግ በጣም አሳዛኝ የሙስና ወንጀል ነው፡፡

2007 ዓ/ም የመንግስት ሠራተኞች በገጠር በከተማ ሳይባል በኑሮ ውድነት ክፉኛ እየተሰቃዩ ባሉበትና እንዲሁም በአንዳንድ የሀገራችን አካባቢዎች ክቡር የሆነው የሰው ልጆች ህይወት በረሀብ እንደቅጠል በሚረግፍበት ወቅት ለጋሞ ጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በ18 ሚሊዮን የህዝብ ገንዘብ አስፓልት መንገድ መነጠፉ ለሰሚ ዘግናኝ ነው፡፡

ጉዳዩን በቅርበት በአይናቸው እየተመለከቱ የሚገኙ የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎችና በተለይ ሁነታውን በደንብ የሚያውቁ የመንግስት ሠራተኞች ፡ በዞን መዋቅር አካባቢ እየተካሄደ/እየሆነ ባለው ነገር እርሪ ድብን ባለ ስሜት " የፍትህ ያለህ " ጥሪያቸውን ለአምላክ በማድረስ ላይ ናቸው፡፡ ነዋሪው የጋሞ ጎፋ ዞን አመራር የሙስና ተግባር በተለያዩ መድረኮች በተደጋጋሚ ያቀረበ ቢሆንም መንግስት ተገቢውን እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ በሙሰኞቹ የበቀል ምት አናታችን እንዲኮረኮም በማድረጉ ጥሪውን ለፈጣሪ/አላህ ለማድረግ ተገደናል ሲሉ መደመጥ በከተማው የለመደ ክስተት ሆኑዋል፡፡

ነገሩ እንዲህ ነው ፡ የ2007 በጀት አመት ሊዘጋ ቀናት ሲቀሩ/ ሰኔ 2007 መሆኑ ልብ ይሏል/ አስቀድመው በወጠኑት የህዝብ ሀብት የመዝረፍ ስትራቴጅ በአርባ ምንጭ ከተማ ሼቻ ክ/ ከተማ በግምት የ1 ኪ/ሜ አስፓልት መንገድ ወደ አስተዳዳሪው ውብ ቪላ ቤት እንዲሰራ ተደርጉል፡፡ ይህ የአስፓልት መንገድ ሥራ በተለያዩ ሙስና ተግባራት የታጀበ መሆኑ ነገሩን ይበጥ እንዲወሳሰብ አድርጎታል፡፡

ከዚህ የአስፓል ሥራ ጋር በተያያዘ መላው የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎችን እንደሚከተለው አነሳለሁ፡-
1. የመንግስት የግዥ አዋጅ ማነኛውም የመንግስት የዕቃና አገልግሎት ግዥ ዋጋ ከ ብር 1500 በላይ በሚሆንበት ጊዜ ግዥው በግልጽ ጫረታ እንዲፈጸም ይደነግጋል፡፡ ይሁን እንጂ የዚህ የ18 ሚሊዮን ብር የአስፓል መንገድ ግንባታ ሥራ ከጫረታ ውጪ ለአንድ የግል ኮንትራክተር እንዲሰጥ ተደርጉዋል፡፡ ለምን? ህዝብ ምላሽ የሚፈልገው ጥያቄ 
2. በጋሞ ጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪነት አቻ በማይገኝለት ፡ ለአርባምንጭ ከተማን የቆየ ገጽታ በመቀየር የሚታወቁት( የነነነ ገባያ ማዕከል በማስገንባት ፡ የተለያዩ የከተማዋ ቀበሌያት የውስጥ ለውስጥ አስፓል ግንባታ ዕቅድ በማቀድና ወደ ተግባር በማሸጋገር ለከተማዋ ዕድገት አይነኛ ሰው በነበሩት በአቶ ዳሮት ጉልማ ዚጌ በ1999 ዓ/ም የ20 ኪ/ሜ የውስጥ ለውጥ የአስፓልት መንገድ ግንባታ ዕቅድ ጸድቆ ነበር፡፡ በዚህ የእቅድ ዝግጂት ወቅት መላው የከተማዋ ነዋሪዎች ፡ የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሠራተኞች እና ከሁሉም የወረዳ አስተዳደሮች የአርሶ አደሩ ተወካይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ነበረ ሲሆን ዕቅዱም የግንባታ ሥራ የሚካዲበት አካባቢዎች በቅደም ተከተል ያስቀምጣል፡፡ በዚህ የ20 ኪ/ሜ የውስጥ ለውስጥ የአስፋልት ግንባታ ዕቅድ የተያዘው (ቅደሚ ተከተላቸውን ባላስታውስም) የነበረው ፡ ከጋሞ አደባባይ በኮንሶ ሰፈር አድርጎ ሄስፒታል ማዞሪያ፡ ከ 03 ቀበሌ መብራት ኃይል አባ ጉተማ ፡ ከገበያ ሰፈር ወደ ስታድየም፡ ከመረብ ብረታ ብረት በ 04 ቀበሌ አድርጎ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ፡ ከውሃና ፍሳሽ አገልግሎት በሀይላንድ አድርጎ በቀለ ሞላ ሆቴል፡ ከመድኃኒአለም ቤ/ያ ወደ ቤተ መንግስት ፡ እና ከሲኖዶስ ተነስቶ ሼቻ ክሊኒክ ፡ ከኃይሉ ጌታነህ ሆቴል ወደ በቀለ ሞላ መንገድ የሚዘቁ መንገዶች ሲሆኑ በአሂን ሰዓት አብዛኛው መንገድ ግንባታ አልተጀመረም፡፡ በርግጥ እነኝህ መንገዶች ሲመረጡ ታሳቢ ካደረጉዋቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል ፡- የየአካባቢው የነዋሪ ህዝብ ብዛት ፡ የመንገድ አገልግሎቱ የሚያገናኛቸው የክፍለ ከተማና ክፍለ ከተማ ፡ የቀበሌና የቀበሌ ፡ የቀበሌና የጎጥ ፡ የጎጥና የጎጥ እንዲሁም የከተማ ነዋሪዎች የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መሰረተ ልማቶች አቀማመጥ ፡ ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ይህ በህዝቡ ቀጥተኛ ተሳትፎ የፀደቀው የውስጥ ለውስጥ አስፋልት ግንባታ ዕቅድ ተግባራዊ ሆኖ ሳያልቅ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ቀጥተኛ ተጠቃሚ ለማድረግ በታሰበ መልኩ የአስፋልት መንገድ ግንባታ እየተፋጠነ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ሁሉም የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪ ሊመለስበት የሚገባው ጥያቄ ፡ ይህ በነዋሪው ከፀደቀው የአስፓልት መንገድ ግንባታ ዕቅድ ውጪ የሆነው መንገድ ቀድሞ እንዲገነባ ለምን አስፈለገ ? 
3. ውድ አንባቢያን ይህ የመንገድ ግንባታ ከሼቻ ቁጠባ ወደ አቶ ጥላሁን ከበደ መኖሪያ ዕንቁ ቪላ የሚወስድ ሲሆን አካባቢው አዲስ ምርትና ነዋሪው ቤት ገንብቶ በስፋት እንኳን ያልገባበት መንደር ነው፡፡ በተቃራኒው ደግሞ የአርባ ምንጭ ከተማ ነባርና ከላይ የተያዘው የአስፓልት መንገድ ግንባታ ዕቅድ የሚዳስሳቸው መንደሮች እንኳን በዕቅድ የተያዘው አስፋልት ሊገባ ኮብል ስቶን በአግባቡ ባልተነጠፈበት መሆኑ ግንባታው የግለሰቡን መኖሪያ ምን ያህል ታሳቢ እንዳደረገ ያመለክታል፡፡ ነገም እንደ ጥላሁን ያለ ሌላ አስተዳዳሪ እየመጣ የራሱን መኖሪያ ቤት ሰፈር ታሳቢ እያደረገ አስፓልት በሚገነባበት እና ኃላፊነትና ተጠያቂነት በሌለበት አካሄድ : በነዋሪው ተሳትፎ የፀደቀው ዕቅድ መቼ ነው ተግባራዊ ሚሆነው ?

በዚህ እና በሌሎች የዞኑ አመራር የሙስና ወንጀሎች ብዙ ብዙ ማንሳት ይቻላል፡፡ ነገር ቢበዛ በአህያ አይጫንም ሆነና በሰሚ አልባ ከተማ አበቱታው ለፈጣር/አላህ ሆኖ ቀረ፡፡

ይህን የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪ ህዝብ ጩሄት ምላሽ ማግኘት አለበት የሚል ማንኛውም የመንግስት አካል በተለይ በተለይ የፌዴራል መንግስት ጉዳዩ በክልሉ መንግስት የሚፈታ መሆኑን አውቆ ጣልቃ እንዲገባ እንጠይቃለን፡፡

ሙሰኞች ለህግ ይቅረቡ
ሕዝብ ምን ጊዜም አሸናፊ ነው

     Give your opinion.