Discussion Forum

 የነገሩ መንስኤ“ኑኒ እሲኖ!

የነገሩ መንስኤ“ኑኒ እሲኖ!
በቅርቡ አንድ ጥገኛ! ከፊውዳል ቤተሰብ የተወለደ! ማንነት የለሌው! ኃይማኖት የለሌውና ከፈጣሪ ጋር የተጣላ አንድ ግለሰብ ሰይጣናዊ ሥራ በመስራት ቁጣ እና ውዝግብ ፈጥሯል፡፡ ነገር ግን የግለሰቡ እኩይ ተግባር በሰከነ እና በህጋዊ መንገድ ብቻ ለማስኬድ ስንል በሳምንቱ ውስጥ የተለያዩ ወሬዎች ስናፈሱ በገጻችን ላይ ምንም ዓይነት አስተያየት አልሰጠንም፡፡
ቀጥሎም ግለሰቡ ብሎአል የተበሉ ዋና ዋና ነጥቦች፡ -
• ህጋዊ ዕውቅና ይዞ በየደረጃው ባለው መዋቅር ተገቢውን ውክልና አግኝቶ የሚኖሩ ብሔሮችና የብሔረሰቦችን መብት ይጋፋል፤ የሉም ይላል፡፡ በተለይ ስሙም ማላ ዶጋላ (ማዶላ) ተብሎ አንድ ብሔር ሊፈጠር ይገባል ይላል፡፡
• አንዳንዱን ሞራል በሚነካ መልኩ ይሳደባል፤ ያንቋሽሻል፤ በተለይ ጋሞ ብሔር፣ ማሌ እና በጐፋ ብሔረሰብ ገዞ ማህበረሰብን ይሳደባል፤
• አሁን ያለውን ደቡብ ክልል በአራት ይከፍላል፣ መዋቅር እንዲጠየቅ ያደርጋል፤
• ኃይማኖት እኩልነትን የማይቀበል፣ ኦርቶዶክስ ከባዕድ እምነት ጋር ተደባልቆ ህዝቡን ግራ እንደሚያጋባ ፕሮተስታንት ደግሞ ነጻ አውጪ እና ፍጹም አዳኝ እንደሆነ ጽፏል፣”
እኔ ደግሞ የሚለው እንዲህ ነው።
የአካባቢውን ሰላም ለማረጋጋት ቁጥጥር ማድረጉ ጥሩ ነገር ሆኖ ሳለ ነገር ግን አንድ ሰው በፍርድ ቤት ደረጃ ውሳኔ አግኝቶ ከተፈረደበት ብቻ ነው ወንጀለኛ ማለት የሚቻለው። ሳይፈረድበት ግን መዓት ስም ስጥቶ ሰውን ማዋረድ ራሱ ወንጀል ነው። በተለይም ጥገኛ፣ ከፊውዳል የተወለደ፣ ማንነት የለሌው፣ ሃይማኖት የለሌው፣ ከፈጣሪ ጋር የተጣላ ሰይጣን ብሎ ወንጀለኛነቱ ሳይረጋገጥ ቀርቶ ወንጀለኛ ቢሆን እንኳን ይህን አይነቱ አስጸያፊ ኢ፟-ሰባአዊ አባባል ከአንድ ከመንግሥት ተወካይ አፍ አንጠብቅም። ፈጽሞ አይባልም። ለሰውዬው ሳይሆን ለሕዝቡ ለራሱ ይህን ያለው ባለሥልጣን ወይም የመንግሥት ተወካይ ይቅርታ ጠይቆና ራሱን በራሱ ከሥራው ማሰናበት አለበት ባይ ነኝ።
ይህንን ጉዳይ አንስቶ አንድ በፈስ ቡክ የሚወደው ጓደኛዬ አቶ ወንድማገኝ አንጁሎ (በፖለቲካዊ አመለካከቱ ከኔ የተለየ አቋም ያለው የተቃዋሚዎች ደጋፊ) (ፖለቲካ ሌላ ወንድማማችነት ሌላ ሆኖ) July 6, 2015 ለጥፎት ነበር። እኔ መጽሃፉን በተመለከተ የማውቀው ነገር የለኝም። አላነበብኩትም። በአገላለጹ ለአካባቢዬ ካለኝ ፍቅር የተነሳ ንደት እንደመስበቅ ሞካክሮኝ ነበር። ከሳምንት በኋላ ደግሞ ይሄው ድፍን የጋሞ ጎፋ ሕዝብ የቀለጠ ትልቅ ወሬ አድሮጎታል። ነገሩ በወቅቱ መቀጨት ያለበት ከሆነ አዎ ጊዜ ሊሰጠው አይገባም።
እዚህ ላይ እኔ የሚለው፣ ሌላው ሰው ከነወንድማገኝ ቀድሞ እንዴት አልለጠፈውም? ቀድሞ ለምን አልተናደደም? ለምን ይህ ነገር ከአቶ ወንድማገኝ ጽሁፍ በኋላ እንዲህ ሊግል ቻለ?
ከአቶ ወንድማገኝ ጋር ብዙ ጊዜ በፖለቲካዊ አመለካከቱ ተፈታትገናል። እርሱ የሚለው ኢትዮጲያ የምትባል አገር ከላይ ወደታች የምትፈጠር ነገር ግን ከስር ወደላይ የምትፈጠር አገር አይደለችም ባይ ነው። አጼ ሚኒሊክ ለርሱ (ለደቡብ ሕዝብ መዋረድ ምክኒያት የሆነው ሚኒሊክ) የርሱ አድራጊና ፈጣሪ እሚዬ ሚኒሊክ ነው። በርካታ አክራሪ የሆኑ የመንግስት ተቃዋሚዎች ቡድን ውስጥ ያለ ወንድም ነው። በምርጫው ኪሳራ እጅግ ከፍተኛ ቅሬታ ያለው ሰው ነው። ታዲያ ይህ ጉዳይ እኔ ሳየው አዎ መጽሐፉን ጻፊ ግለሰብ ወንጀል ሰርቶ ይሆናል እኔ አላውቅም። ጸሐፊውም ሆነ ቀዳሚ ከሳሾቹ ለጋሞ ጎፋ ሕዝብ ፍላጎት (for the best interst of Gamo Gofa people) ቅድሚያ ሰጥተው ያደረጉት ነገር ምን አለ ተብሎ በዝርዝር መታየት አለበት። እነዚህ የመጻሐፉን ጻሐፊ ቀድመው የከሰሱት እነወንድማገኝ አንጁሎ የምርጫውን ኩርፊያ ለመበቀል ከሆነስ? በርግጥ አዎ ተቃዋሚ ነን ግን በቅን ለጋሞ ጎፋ ሕዝብ ስንል ይህንን በእውነት ተስምቶን ነው ስለማለታቸው ምን ማረጋገጫ አለን?
አሁን ላለንበት ነጻነታችን መገኘት የሁላችንም መስዋዕትነት ተክፍሎአል። በሁላችንም ድካም የተገኘ ድል ነው። አሁን እንኳን በውጪው አለም የምንከፍለው መስዋዕትነት ይህ ነው አይባልም። ጠላቶቻችን በስራችን፣ በኑሮአችን፣ በልጆቻችን ላይ ስንት ጉዳት እያደርሱብን ግን ትግሉ ለአገራችንና ለሕዝባችን ልማትና ዕድገት ስለሆነ ሌት ተቀን እንለፋለን። ታዲያ ውጤታችን ከላይ ያለውን ሕገ-ወጥ አባባሎች የመሳሰሉትን በሚሰነዝሩ አለቆቻችን ትግልችንና ልማታችን ሊደናቀፍ አይገባውም።
የአቶ ወራባ እራሻ ጎተና አጻጻፍ መነሻ ሊኖረው ይችላል። ከተሳሳትኩ አርሙኝ።
ከምርጫው ጋር በተያያዘ መልኩ በሕዝቡ መሀል ሁካታ ለመፍጠር ያመቻል ብሎ አስቦ ሊሆን ይችላል።
በጋሞ ጎፋ ሕዝብና በወላይታ ሕዝብ መሃከል ያለውን የዱንጉዛን ጥያቄ ለማደፋፈን ሲል ሕዝቡን ማጋጨቱና መከፋፈሉ አማራጭ ይሆናል ብሎም ሊሆን ይችላል።
እውነትም ነፍጣኝነቱ በነውጥነት ተጠናውቶት ሕዝቡን መበተን አለብኝ ብሎ ይሆናል።
በነገራችን ጋሞን ከጎፋ፣ ከቁጫ፣ ከቦረዳ፣ ከዳውሮ፣ ከወላይታ፣ ከካምባታ፣ ከኮንታ፣ ከማራቆ፣ ከኮይራ፣ ከበስከቶ፣ ከሃዲያ፣ ከዲመ፣ ከከፍቾ፣ ከማሌ፣ ወዘተ… ለመለየት ማሰብና መበተን ራሱ ትልቅ ወንጀል ነው። በአፄ ሚኒሊክ ጊዜ ነበር ህዝባችን በአራት ቦታ ማለት ዳውሮው፣ ዲመው፣ ከፍቾው ወደ ከፋ ክ/ሃገር፣ ከንባታው ማራቆውና ሃዲያውን ወደ ሸዋ ክ/ሃገር፣ ወላይታውንና ኮይራውን ደግሞ ወደ ስዳሞ ክ/ሃገርና ጋሞውን፣ ጎፋውን፣ ማሌውን፣ በስከቶውን፣ ቁጫውን፣ ቦረዳውን፣ ከንባውን፣ ኮንሶውንና፣ ደቡብ ኦሞውን ጨምሮ እንደ አንድ ክ/ሃገር አድርጎ በመክፈል አቅም እንዳይኖረን ተደርገን ቀጥ ለጥ ብለን ተገዛን። አሁን ያ አይነቱ ንትርክ ቦታ የለውም። አዎ አንድ ሕዝብ ነን።
አዎ አንድ ነን ሲል ደግሞ የአቶ ወራባ እራሻን እየደገፍኩ ነው። እዚህ ላይ አዎ አቶ ወራባ እራሻ የሚለው አንድ ትክክለኛ ሃሳብ አለ። አሁን ያለውም መንግሥት ሆነ ማንም ሊሰነጥቀው የማይችለው አንድ ቁም ነገር አለ። ይህም “ጋሞ፣ ጎፋ፣ ወላይታ፣ ዳውሮ፣ ኮንታ፣ ባስኬቶ ወዘተ…የሉም አንድ ብሔር ናቸው፡፡” የሚለው አባባል ነው። እኛ አፍሮ ኢሲያትክ ወይም ኦሞትክ ሕዝቦች የዘር ግንዳችን አንድ ነው። አዎ ማላ ዶጎላ ከጥንት ጀምሮ ያለ የማህበረስብ የዘር አመጣጥ ግንድ ነው። ማላና ዶጎላ መጠራት የጀመረበትን ጊዜ በውል ባልውቅም ይህ ሕዝብ ለአሥር ሺህ አመታት በዚሁ ከልል እንደኖረ እንዲያውም የደቡብ ሕዝቦች ድንበር ከጎጃም ዳሞት ጀምሮ እስከ ማሌና መስከቶ ድረስ እንደሚደርስ ታሪክ ይናገራል። ከምድሪቱ ጋር አብሮ የተፈጠረ ሕዝብ ነው። በዚህ አባባሉ አቶ ወራባ እራሻ ትክክለኛ ነው።
ነገር ግን በአስተዳደር ክፍፍሉ ውስጥ ገብቶ ሕዝብን ማነታረኩ፣ መሳደቡና ማዋረዱ ተጨምሮበት እንደሆን አግባብ አይመስለኝም። ሕገ-ወጥ ነው። ዋናው ቁም ነገር “አማራ ተፈናቀለ የሚያስበል ዘመቻ እንዳያስከትልብን አቅርቦ በመወያየት ችግሩን መፍታቱ ከእስርና ውጣ ውረድ የተሻለ መፍትሄ ይመስለኛል። ሌላው ስልጠቅሰው የማላላፈው ነገር፣ በየትኛውም ከፍል ይሁን በየትኛውም በደቡብ ከልል ከብሔረሰቦች ማንነትና ምንነት ጋር ተያይዞ ባለ ጉዳይ የታሰረ ማንም ሰው ነጻ መውጣት አለበት። ጊዜ የማይሰጠውና አለጊዜ ቀጠሮ ወደቤታቸው የሚሄድበት መንገድ ቢኖር ለወድፊቱ አሥራርና አስተዳደር ቀና በር ይከፍታል። ይህ የቁጫ፣ የጎፋ ችግር የሚባለው ነገር በፍጹም ሊከሰት አይችልም። ሕዝቡ ደሞኪራሲ መብቱን ገና ሀ ብሎ መቀመስ እየጀመረ ስለሆነ አስተምሩት እንጂ ይህንን የዋሁን ሕዝብ ራሳችሁ ከየዋሁ ሕዝብ እምብርት የተፈጠራችሁ ሆናችሁ በቅንነት ምሯቸው አደራ። የፖለቲካው ስልጣን ለግለሰቦች ኢኮኖሚያዊ ጠቀመታ ሳይውል ለሕዝብ ለራሱ ፍላጎት በቀጥታ ሊውል ይገባል ባይ ነኝ።
እኔ በሚኖርበት ካናዳ ውስጥ አንድ ኩበክ የሚባል ክ/ሀገር በየጊዜ የመገንጠል ጥያቄ ያቀርባል። አንድም ሰው አንድም ቀን ታስሮ አይውቅም። ነገር ግን ሁልጊዜ በህዝብ ድምፅ ይወድቃል። የዚህ አይነት ሁኔታ ከተፈጠረ ደግሞ ሕዝበድምፅ እንዲሰጥ አድርጎ ውድቅ ማድረጉ የዲሞኪራስውን ምህዳር ያሰፋል በዬ አምናለሁ።
የደቡብ ሕዝቦች ዕንባ መረሳት የለበትም። ከዚህ ቀጥሎ ያለውን ልብ ብላችሁ አንብቡት። ስይጣናዊው ነፍጥ በሕዝባችን ላይ ያደረሰውን ስይጣናዊ በደል።
ስለሃይማኖት አቶ ወራባ እራሻ ያለውን ዝርዝር ሁኔታ ባላውቅም የሃይማኖት ጥያቄ በጣም አስቀያሚ ችግር የፈጥራል። ጥንቃቄ መደረግ ያለበት ጉዳይ ነው። በተለይ በስልጣን ላይ ያለው ማንም ሰው የሃይማኖት ወሬ ማውራት ተገቢ አይደለም። በታሪክነቱ ካየነው ግን እንዲህ ነው ነገሩ። ከ12ኛው ከ/ዘመን ጀሞሮ ነው ሃይማኖት ወደደቡብ የመጣው በኦርቶድክስ ሚሺነርዎች አማካኝነት። ከዚያም ደግሞ በ1920ዎቹ ገደማ ነበር እንተርናሺናል ሚሽነሪ ወደኢትዮጲያ የገባው። በዚህም ጊዜ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት በደጋማው ክፍል በርካት በተክርስቲያናትን ከመስራቱም አልፎ ከአፄ ሚኒልክ ጦር ጋር የመጣው ቀሳውስትና መነኩሳት በአስተዳደሩ ላይ ብቻ ሳይወሰኑ መሬት ከመቀራመቱ አልፎ እስክፍርድቤት ዳኝነት ድረስ ድርሰው ነበር። አዎ የበተክህነት ስዎች በኛ ሕዝብ ላይ ሲፈርዱ ነበር። በአንድ አውስትራሊያዊ ሚሺነሪ (Mr. Dick McLellan) በቦታው የነበረ የአይን ማስረጃ) በተጻፈ መጽሐፍ ገጽ 21 ላይ ስንመለከት ስለአንድ አቶ ማሄ የሚባሉ ስለወላይታ ሰው እንዲህ ሲል ይናገራል። በጥር 1947 ዓም በጎፋ ቡልቂ ከተማና ቁጫን ጨምሮ ለ27 ጊዜ ታስረዋል ይላል። አሳሪዎቹና ከሳሾቹ የኦርቶዶክስ በተክርስቲያን ቄሶች ነበሩ። መፅሐፉ በጥሬው እንዲህ ሲል አስቀምጦታል። (“Mahe had shackles on his wrists and aroung his ankles. The chains rattled when he moved. His clothes were ripped and splattered with blood. His face was puffed up, his lip was split and had lost quite a bit of skin from a savage beating, and he had endured overnight. Large drops of blood dripped onto his shoulder from an open head wound. There was cuts bruises all over his body and he was obviously in a lot of pain”) ይላል። ሌላው ደግሞ አቶ ደፈርሻ ነበር። እርሱ ደግሞ በነፍጠኛ ታጣቂዎች ተከቦ ከኦይዳ ቀበሌ ተይዞ ለአረብ የባሪያ ነጋዴዎች የተሰጠ ሰው ነው። ደፈርሻን የወሰዱት የአረብ ነጋዴዎች በጎንደር ውስጥ ላሌ ለአንድ ሐብታም ሰው ሸጠውት ግን ደፈርሻ አምልጦ ለሶስት ወራት ተጉዞ ኦይዳ የተመለስ ሰው ነበር። ድፍን የደቡቡ ሕዝብ ጸሃይ ካልወጣ በስተቀር ወድ ውጪ ሳይወጣ ነበር ተደብቆ የሚያድረው። በአንድ ቀን ብቻ ወደ40ሺህ ሰው ከዳውሮ አካባቢ ታፍሶ እንደተወሰድ ነው ታሪክ የሚናገረው። በዚሁ መጽሃፍ ገጽ 39 ላይ የሚገኘው አቶ ቃባ ነበሩ። እርሳቸውም ታስረዋል ይላል። ሌሎቹንም እነ አቶ ላሊሶ፣ አቶ ተቃ፣ አቶ ናና፣ አቶ ዳንጎ፣ አልዳቦ፣ ጀማሬ ወዘተ ብንመለከት በኦርቶዶክስ ቄሶችና ጀሌዎቻቸው ታስረዋል፣ ተገርፈዋልም።
በቡልቂ ፍ/ቤት ውስጥ አቶ ማሄና Mr. Dick McLellan አንድ ላይ በቆሙ ጊዜ እንዲህ ነበር የሆነው።
“A few years after our first meeting, Mahe and I stood together as prisoners in the Bulki courtroom. Three angry judges, an even angrier priest from the Ethiopian Orthodox church, several court officials and the police prosecutor all shouted at us together. A great wave of prosecution was sweeping over Gofa. Church building were burnt down, the Christian houses looted, the animals stolen, dozens of elders arrested.”
በድርግ ጊዜም ቢሆን እነዚሁ ስዎች ሰዎቻችንን አሰቃይተዋል።
እኔና የቅርብ ጓደኛዬ አቶ ዳዊት አይካ ሆነን እግዚአብሔርን በአንድ ቦታ እያመለክን እንዳለን ነበር የቀድሞ ጊዜ አስራለቃ ልጅ የነበረና በወቅቱ የድጎማ አስተማሪ በጠመንጃ አስፈራርቶን ከቦታው አባረረን፣ በዚህ አላበቃም፣ እስራቱና ስደቱ ስለበዛ ከሚኖርበት ከምራብ አባያ ከተማ ሽሽቼ ሌላ ቦታ ሄጄ ጊዜየን ማሳላፈን አስታውሳለሁ። አጎቴ 1 አመት ከ8ወር፣ ልጃቸው ሚልኪያስ ለ8 ወር አለወንጀል መታሰራቸው፣ ጨንቻ ጦሎላ ያለው በተክርስቲያን ለጎማጣ ሲሰጥ እዚያ ያሉትን መሪዎቹን በሙሉና በየአውራጃው ያለውን የቃለሕይወት በተክርቲያን መሪዎችን በመሉ ለእስር ዳርገው ነበር። አሳሪዎቹ በሙሉ የቀድሞ ባለሥልጣናት ልጆች ካድሬ ለደርግ በመሆን (የባላባት፣ የጭቃ ሹም፣ የምስለነ፣ የዳኛ፣ የቀኛዝማች፣ የደጃዝማች፣ የበተክህነት መሪዎች) ነበር።
ስደቱ በዚህ አላበቃም። የጎልማሶች ማሰልጠኛ ጣቢያ ሳገለግል ከአልዱባ ሚሺነሪዎች ጋር በመሆን አንዲት ትንሽ የሳር ቤት በተክርስቲያን ሰርተን ነበር። በተክርስቲያንቷን ብቻ ሳይሆን ለአማቼ የሰራኋትን ቤት ጭምር ነበር ያቃጠሉት። በገዛ አገራችን አገር አጣን። አሁንም ታሪኩ ከዚህ በጣም የራቀ አይደለም።
ይህን ቀጥሎ ያለውን እንመለከት። https://youtu.be/SuOAGHnS5Mk በሚታየው ቪዲዮ ላይ ያለውን ትይንት የሚሠራው ዶ/ር ታደስ ወልዴ ነው። ይህ ሰው አባቱ ሕዝባችንን አስሮና አሳቃይቶ ካለፈ በኋላ የጋሞ አካባቢ ሁዱግ በመሆን ተሹሞ ሕዝባችንን እርስ በርስ በሃይማኖት ሳቢያ ሲያዋጋ እናያለን። ዶ/ር ታደሰን የአካባቢው ሁዱጋ ሊያደርገው የሚችል አንድም መለኪያ የለም። ዶ/ሩ በአባቱ ጎንደሬ ነው። ታዲያ በምን ቤት እርሱ ጋሞ ላይ ሁዱጋ ይሆናል? ከበተሰቦቻቸው የለመዱትን እኩይ ተግባር አሁንም አልተውትም። ዶ/ር ታደሰን እዚህ ካናዳ በመጣ ጊዜ የድሮ ት/ቤቶችን እንዲያስጠግንልን ለምኜ እሺ ብሎ ከሄደ በኋላ እርሱ ግን በተክርስቲያናትን አስጠግኖና ለጎደኞቹ የዩኒቬርሲቲ መማሪያ ገንዘብ በለንደን ኦክሽፎርድ ዩኒቬርሲቲ ከፍሎ አረፈ። የዶ/ሩ ስራ ይህ ብቻ አይሰለም ብዙ አለ ግን ለግዜው ይብቃኝ።
ይህ አይነቱ ነገር እንደገና እንዳይከስት ሕዝባችንን ወካላችሁ ያላችሁትን በመሉ አደራ እላለሁ። በተለይም የፕሮተስታንት ሃይማኖት መሪዎች በቀድሞ ጊዜ የባሕል ሃይማኖቶች የሚከበርባቸው ቦታዎች ጥሩም ባሕል ይኑረው መጥፎ ባሕል፣ ቁም ነገሩ ታሪካችን ነው መከበር አለበት። ለአመታት መተላለፍ አለበት። ሃይማኖት በግልበት አይደለም፣ በእልክ አይደለም፣ በመግፋት አይደለም፣ ናጋሳ ዶርቦ አናቱ ላይ በተክርስቲያን በመሰራቱ ልዩ ነገር ሊፈጠር አይችልም። ታሪካችን ቅርሳችን ልጠበቅና ለዘለአለም ሊኖር የሚገባ ነው። በብርብር ማሪያም፣ በሱልአ፣ በወላይታ፣ በቁጫ፣ በቦረዳ፣ በምዕራብ አባያ አካባቢ፣ በርካታ ዘመዶች አሉኝ። ግማሾቹ ፕሮተስታንት አብዛኞቹ ኦርቶዶክሶች ናቸው። እኛ ላንፋት ተጋብተናል። ኦርቶዶክሱ ቢጎዳ እኛው ነን። ፕሮተስታንቱ ቢጎዳም እኛው ነን። ካሻችን ቢውድም እኛው አሁንም ተጎዳን። መቻቻል (ቶሌራንስ) ሊኖር ይገባል። አዎ የፕሮተስታንት ሃይማኖት ከወለጋ ጀምሮ እስክ ኦይዳ ድረስ ያለውን ሕዝብ በትምህርትም ይሁን ከባርነት ነጻ አውጥቶአል። አቶ ወራባ እራሻን በዚህ ሃሳቡ እደግፋለሁ።
ኢትዮጲያ ለዘለዓለም ትኑር። ደቡብም እንደዚሁ።

     Give your opinion.