Discussion Forum

 አቶ ታገሰ ጫፎ፣ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል የአቅም ግንባታና የመልካም አስተዳደር ኃላፊ ከርፖርተር ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ

አቶ ታገሰ ጫፎ፣ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል የአቅም ግንባታና የመልካም አስተዳደር ኃላፊ ከርፖርተር ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ውስጥ ያልተመቸኝን በቀሳ መልክ እነሆ ለአንባቢዎቻችን ለማቅረብ እሞክራለሁ።
አቶ ታገሰ ጫፎ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር በመሆን ለአሥር ዓመታት አገልግለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከተመሠረተ ሁለት ዓመት የሞላው የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የአቅም ግንባታና የመልካም አስተዳደር ዲፓርትመንት ኃላፊ ናቸው፡፡ አቶ ታገሰ ቀደም ሲል በከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ውይይት የተደረገበትን በመልካም አስተዳደር ችግሮች ዙሪያ የተሠራውን ጥናት ያስተባበሩ ሲሆን፣ በጥናቱ ግኝትና በወቅታዊ ችግሮች ላይ የርፖርተር ጋዜጤኛ የማነ ናግሽ በMar, 19,2016 አነጋግሯቸዋል፡፡ በዚህ ቃለምልልስ ስለዲሞኪራስ ምላሻቸው ላይ የሚከተለውን ብለው ነበር።

tagese chafo


የሚከተለው የርስዎ አባባል ነው። “ለምሳሌ የምሥራቅ እስያ አገሮችን ተሞክሮ ያየን እንደሆነ፣ በልማታዊ መንገድ ከእነሱ ተሞክሮ መውሰድ እንችላለን፡፡ ከዲሞክራሲያዊነት አኳያ ከእነሱ ተሞክሮ መውሰድ አንችልም ብለን በግልጽ አስቀምጠናል፡፡ የታይዋንና የኮርያን ልምድ በምንወስድበት ጊዜ እነዚህ አገሮች የማንነትም የእምነትም ብዝኃነት የላቸውም፡፡ አንድ ብሔርና አንድ ዓይነት እምነት የሚከተሉ ናቸው፡፡ ስለዚህ እነዚህ አገሮች ፀረ ዴሞክራሲም ሆነው ልማትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሁኔታ ነበራቸው፡፡ በእኛ ሁኔታ ግን የሚያስኬድ አይደለም፡፡ ረጅም ትግል የተካሄደው አንደኛው በማንነት ጥያቄ ላይ ነው፡፡ ሁለተኛ የሃይማኖት እኩልነት ጥያቄ ነው፡፡ እነዚህን ጥያቄዎች መመለስ የህልውና ጉዳይ ነው፡፡ ከእኛ ሁኔታ አኳያ ደግሞ በሕገ መንግሥቱ መሠረት ነባራዊ ሁኔታዎችን ማስተናገድ የሚል ነው፡፡ ስለዚህ ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንግሥት በሚል ነው የያዝነው፡፡”
በኔ አመለካከት ይሁን በሌላ በዲሞኪራሲ በዳበሩት አገሮች አመለካከት፣ ዲሞክራሲ የአንድ አገር ሉዓላዊ ስልጣን በአንድ አገር ህዝቦች የበላይነት የሚመራ የስልጣን ባሌበትነት ነው። እንዲያገለግል ተብሎ የተመረጠው አካልም ቢሆንም ተጠሪነቱ ለመረጠው ህዝብ ነው። ይህ የህዝቦች የበላይነት ማንም ሊገረሥሰው ወይም ሊንደው የማይቻል ወይም ሆን ተብሎም በአቋራጭ ኪስ ውስጥ የሚገባ የባንክ ብድር ወይም ለአንድ ጉሳና ለአንድ ቡድን በሞግዚትነት፣ በውክልና፣ በጥብቅናና በውሰት የሚተላለፍ ዕቃ ወይም ገንዘብ አይደለም። ህዝቦች ሊፈሩት የሚገባውም ራስቸው ለራሳቸው አገርና ህዝብ በሚመች መልኩ ወደው ለቀርጹት ህግመንግስት ነው። ህገመንግሥቱ እንዲከበርም ዘጎች ከየክልላቸው ራስቸውን እንዲወክል አድርገው ወደው የመረጧቸው ውኪሎቻቸው (የሸንጎው ምክር ቤት) የመረጠውን ህዝብ ወኪለው ክልላቸውን በተመለከት ችግሮቻቸውን አቅርበው ተከራክረው አሳምነውና አምነው የሚሰሩበት መድረክ እስካለ ድረስ ህጉ ይከበራል እንጂ ማንም ሊቦርሸው አይችልም። ያ ማለትም በአገሪቱ ውስጥ ያለው ማናቸውም አሰራር በቀላሉ በቁጥጥር ስር ሊውል ይችላል። ህገመንግስቱ በቂ አይደለም ከተባለም ሌላ አዲስ ህግ በህግ አውጪው ክፍል በማከልና ጊዜ ያለፈባቸውን ህጎች በመሰረዝ (repeal) በማድረግ ለህዝቦች ጥቅምና ለአገሪቷ ሉ ዓላዊነትም ጭምር ምቾት በሚሰጥ መልኩ እየተደነገገ ለመሠረታዊ ህዝቦች ጥያቄ ዋስትና የሚሰጥ አለኝታ መሆን አጠያያቂ አይመስለኝም። ይህ ማለትም እያንዳንዱ ዘጋ እንደፈለገ ወጥቶ የሚገባበትና የሚወጣበት ከእልክና ከትዕቢት ነጻ የሆነ ማናቸውንም ነገሮች በህግ መንግስቱ ላይ መሠረት በማድረግ የሚራመድ አገርና ልማቱም ሆነ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ሂደቱ እንቅፋት ሳይኖረው አንዱ ካቆመበት ሌላው የሚቀጥልባት ሰላማዊ አገር እንደሚሆን ዝርዝር ዘገባ አያስፈልገውም።
ዛሬ በአገራችን ያለው መንግስት እርስዎ እንዳሉት የኮሪያ፣ ወይም የታይዋን፣ ወይም የቻይና ወይም የራሺያ፣ ወይም የአልበኒያ፣ ወይም የኩባ ካልሆነ፣ የኛ አገር ዲሞክራሲ የየትኛውን አገር ዲሞኪራሲያዊ መመሪያ የተከተለ ነው? እርስዎ እንደምሳሌ ስጠቅሱ ለምን የአሜሪካኖችን፣ የእንግሊዞችን፣ የአውስትራሊኖችን፣ የስካንዲነቪያን ወይም አቻ የአፍሪካ አገራትን (በኒን፣ ሴኔጋል፣ ሴራሊዮን፣ ሳውዝ አፍሪካ፣ ታንዛኒያ፣ ሌሰቶ፣ ናሚቢያ፣ ቦትስዋናና ጋናን) የመሳሰሉትን ለምን አልጠቀሱም? ወይስ የኛ ዲሞኪራሲ ከመቀሌ ወይም ከአድዋ ነው? ህዝቦች የመምረጥና የመመረጥ አቅማቸው በካድሬና በጠመንጃ ተቀምቶአል። እርዎም ቢሆኑ ያለውን መንግስት ለስልጣንዎ ሲሉ ህዝቡን ለመሸንገል ካልሆነ በስተቀር እውነቱን አጥተው አይደለም። ለራስዎም በየደቂቃው እንደምዳቋ እየፈሩ እንደሚኖሩ ቅንጣት ያህል ጥርጣሬ የለኝም። ህዝብ የፈለገውን ይምረጥ፣ የፈለውን ያውርድ፣ ነገር ግን የህዝቦች ነጻነት ለህወሃት የተሰጠ ነጻ በረከት አይደለምና ራሳችሁንና ህዝባችንን ከህወሃት ቅኝ አገዛዝ ነጻ ልታዋጡ ይገባል። በናንተ መፍራት ከሥር ያለው ህዝብ (90 ሚሊዮን ህዝብ) እንደሠርዶ ሲደቅ ይታየናል። የኢትጲያ ህዝብ ነጻነት፣ ክብር፣ ንብረትና ሃብት ለአንድ ቡድን የጥቅም ማስጠበቂይ ሊሆን አይገባም። ስለዚህ መልስዎ ለራስዎ ቢመችም ለሰፊው ህዝብ አይመችም። በአጥር ላይ እንደተንጠለጠለው የኤሌክትሪክ ሽቦ በውስጡ ሃይል የለውም ብሎም በየተራራው ላይ በተወጠረው እንደቴሌ ታዎር ነትዎርክ የለሌው ባዶ ገለጻ ሆኖ አግኝቸዋለሁ። ገላጻዎ በመምረጥ እንጂ በመመረጥ (selected not elected) እንዳሆነ አያብራራም። ለምን ህዝብ ይሸማቀቃል በገዛ ካርዱ?
ወደሁለተኛው ነጥቦው ሊሸጋግርና ስለማንነት ጥያቄ አስመልክተው የሚከተለውን በለዋል። የሚከተለው የርስዎ አባባል ነው።
“በዚህ አገር ረዥሙ ትግል የተካሄደው ለብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት ጥያቄ ነው፡፡ ብዙ መስዋዕትነት የተከፈለበት ጥያቄ ነው፡፡ በሕገ መንግሥቱ በዝርዝርና በግልጽ ተቀምጧል፡፡ ዛሬ ከ20 ዓመታት በላይ ሆኗል፡፡ የአገራችን ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ዕውቅና አግኝተዋል፣ እያገኙም ይገኛሉ፡፡ ይኼ ሆኖ ሲያበቃ ሕዝብ ያሉት ቅሬታዎች መነሻ ይደረግና አንዳንድ አካባቢዎች ልዩነት በግድ ተፈልጎ ‹ልዩ ነን› የማለት ዝንባሌዎች አሉ፡፡ ሕዝብ ውስጥ ተወርዶ ሲጠየቅ ትምህርት ቤት አልተሠራልንም፣ መብራት የለንም፣ ፍትሕ የለም፣ አልተጠቀምንም የመሳሰሉ ጥያቄዎችን ያነሳል፡፡ በሌላ በኩል ሕዝቡ ውስጥ ያለውን ቅሬታ በመኮርኮር፣ ‹‹እኛ ልዩ ሆነን ብንወጣ እንዲህ ይሠራልን ነበር …ወዘተ›› እያሉ የማንነት ጥያቄ ለማራገብ የሚሞክሩ ኃይሎች አሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም በአጽንኦት እንዳሉት እንዲህ ዓይነት ሥራ ገንዘብ የመሰብሰቢያ መንገድ ሆኗል፡፡ ስለዚህ በዋናነት መሠረታዊ የሆኑ የማንነት ጥያቄዎች ተመልሰዋል፡፡ ዕውቅና አግኝተዋል፡፡ ለምሳሌ እኔ የተወለድኩበት ጋሞ ጎፋ ዞን በርካታ ብሔረሰቦች ያሉበት አካባቢ ነው፡፡ አምስት ነባር ብሔረሰቦች አሉ፡፡ አንዱ ጋሞ ብሔረሰብ ነው፡፡ ኢሕአዴግ ሥልጣን ይዞ 20 ዓመታት ካለፉ በኋላ ‹‹እኛ ልዩ ነን›› ብሎ አሁን ተነስቷል፡፡ የማንነት ጥያቄ ይዞ፡፡ የማንነት ጥያቄ ቢሆን ኖሮ መጀመሪያውንም በተነሳ ነበር፡፡ ከእኛ መዋቅር የወጣ ሰው አሁን ያለውን የአስተዳደር ችግር መነሻ ያደርግና ተመልሶ የማንነት ጥያቄ ማራገብ ላይ ነው፡፡ ሕዝቡ ዘንድ ታች ወርደን ተወያይተናል፡፡ ሕዝቡ አንድ ነው፡፡ ባህሉ አንዱ ነው፡፡ ቋንቋው አንድ ነው፡፡ የማንነት የመጀመሪያ መገለጫ ቋንቋ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያሉት ሕዝቡ የሚያነሳቸውን የአስተዳደር ቅሬታዎች እያራገቡ ለገንዘብ መዋጮ እየተጠቀሙበት ነው፡፡ ይኼ በተጨባጭ መቆም ያለበት ነው፡፡ መፍትሔው ፈጣን ልማት ማረጋገጥ ብቻ ነው፡፡ ይኼ ብዙ ነገር ይመልሳል፡፡ የሕዝቡ የአስተዳደር ቅሬታም እየተፈታ ይሄዳል፡፡ ያንን ተጠቅመው የማንነት ጥያቄ በአጀንዳነት እያራገቡ የሚመላለሱ ሰዎችና ሚዲያዎችም እየከሰሙ ያድራሉ፡፡”
በተለይ ስለጋሞ ጎፋነትዎ በጠቀሱት ሃሳብ ላይ ቅሬታየን አሁንም ለማስቀመጥ እሞክራለሁ። ከዐፄ ሚኒሊክ ጀምሮ የደቡብ ሕዝቦች ተከፋፍለው ዳውሮው፣ ጃንጃሮውና ከፋው በከፋነት፣ ከንባታው፣ ሃዲያውና ማራቆው በሸዋነት፣ ወላይታውና ሲዳማውም በሲዳሞነት ከፈጣሪ እንደተጠ ስጦታ ተቀብሎ እስካሁንም እንደባህልና እንደልማድ እዚያው እያንጯለቀ ህይወቱን በሚገፋበት በአሁኑ ሰአት ማዶላዊያን የሚባሉ የሃስት ነቢያት ተነስተው ጋሞ ጎፋን ለሁለት ለመከፋፈል ሲሞክሩ ህዝቡ አይ እኛ አንድ ህዝብ ነን ብሎ ሰላማዊ ሰልፍ ወጣ እንዲያውም በተዛዋሪ እርሶንና ስራትዎን በግልጽ ለመቃወም ወጣ እንጂ ጋሞነተን ወይም ጎፋነቴን ተቀማሁ ብሎ ሰላማዊ ሰልፍ አልወጣም። እርስዎና እርስዎን የመሳሰሉት ሰዎች እያሉ ነበር የአርባምንጭ ዩኒቬርሲት ለገዛ ወንድሞውም (የተከበሩ ዶ/ር ንጋቱ ጫፎ) ከሚሰሩበት ከዩኒቬርሲቲው አስተዳዳሪነት አለምንም ምክንያት በአንዳንድ ወረበላዎች በተጠነሰሰ ሴራ ተሸማቅቀው ሙያቸውን ትተው ከሙያቸው ውጪ ሌላ ለመኖር ብቻ በሚያስችል ተራ ስራ ላይ የተሰማሩት? እርስዎንና እርስዎን የመሳሰሉት እያሉ ነበር ረ/ፕሮፌሰር ቱማ አየለ አለወንጀል ወንጀል ተደርጎ አንድ የተማረ ሰው ቢፈጠርልን ዛሬ ወይኒ ውስጥ ያን ያህል ጊዜ እንዲማቅቅ ሲደረግ ምን አደረጋችሁ? ሰዎች የማንነት ጥያቄ ማንሳት ሃጢአት ሳይሆን እግ/ር የቸራቸው መብት ነው። ስህተት ከሆነ ተማር ይባላል እንጂ እንደአገር መክዳት ውንጀል ቦታውን ለመውሰድ ሲባል ወህኒ መወርወሩ ዲሞኪራሲያዊ አሰራር አይደለም። እርስዎ እንዳሉት ዕድሉን ስጥተን ቆይተናል ነገር ግን አሁን የሚነሳ ጥያቄ አይደለም ሲሉ በህጉ የተጠቀሰው ህጉ እስካልተሻረ ድረስ ልምምዱ ይቀጥላል ምክንያቱም የዘግነት መብታቸው ነው! ሰዎች ከስራ ሲባረሩ እናንተ ግን ተምችቶአችሁ ከሹመት ሹመት የምትቀያይሩት ምን በጆሮአቸው ሹክ ብላችሁ እንደሆን እኛ ባናውቀም ጊዜና ታሪክ ያጋልጣችኋል። እናንት የምታምኗቸው የትግራይ ወታደራዊ መንግስትም እናንተ ወድዳችሁ ሳይሆን ህዝብ ያላቀፈው ስለሆነ ጅብ ስጮህ እንደሚፈርሰው እንደአህያ ቆዳ ግድግዳ መፍረሱ አይቀረ ነው። እርስዎንና እርስዎን የመሳለሉ እያሉ ነበር መምህር ወንድማገኝ አንጁሎ ባልሰራው ሰራ ለአራት ወራት ወይኒ የቆየው አልፎ ተርፎስ በበተሰቡ አ እሞሮና ህሊና ውስጥ የደረውን ጉዳት ማን ይክሳል? እርስዎና እርሶዎን የመሳሰሉ እያሉ ነበር፣ የቅድሞው አስተዳዳሪ አቶ ጥላሁን ከበደ፣ የኢሰፓ ኦ ሶሪይ ማለት ያሁኑ የኢሃደግ ፓርቲ ተጠሪ አቶ ተሳፋዬ በልጅጌ የሰዎችን ሚስቶች እየደፈሩ የህዝብ ነበረት ሲዘርፉ እሲቲ ምን አደረጋችሁ? በሹመት ላይ ሹመት ስትሰጡ አይተናል። ብዝሃነት፣ ተግዳሮት፣ ጥሩ ወንበር፣ ጥሩ ቤት፣ ብላ ብላ አትበሉ ስልጣን የህዝብ ነውና ለህዝብ ስጡ። ዲሞኪራሲ ማለት ያ ነው!
ለማጠቃለል ያህል፡ - እርስዎ ባሉት መልክ ሳይሆን ስልጣን የህዝቡ ወይም የዘጎች የግል ንበረት ነው፣ የጋሞ ጎፋም ህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ የወጣው አንከፋፈልም በማለት እንጂ ማንነቴ ይታውቅልኝ በማለት አይደለም። ከይቅርታ ጋር እስቲ ስህተትዎን ያርሙት።

     Give your opinion.

Williammigo 2016-05-12

I am so grateful for your forum.Really looking forward to read more. Want more. Gambee