Discussion Forum

 ሌባ በመሰሉ እጅ ሲወድቅ ማየትን የመሰለ እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነገር የለም።”(እፎይታ)

ሌባ በመሰሉ እጅ ሲወድቅ ማየትን የመሰለ እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነገር የለም።”(እፎይታ)
ጭንቅላቱን ውጭ አገር ጭራውን አገር ውስጥ አስቀምጦ በጨረሻዋ ጣዕረሞት ሥቃይ ላይ የሚቃስተው ያረጀውና ያፈጀው የፊውዳሉ ሥርዓት መልኩን በመቀያየር የማይቀርለትን የሞት ፅዋ በመጎንጨት በድጋሜ አይወድቁ ውድቀት ለመቋደስ እየፈጠነ ነው። 
ሆኖም ግን፣ “እኔ ከሞትኩ ሠርዶ አይበቀል” ነውና ከመሞቴ በፊት አገረውን ከነጭራሹ እርስ በርስ አጋጭቼ ነው የሚጠፋው በማለት እልኩን ተያይዞታል። ይህ ዓላማቸው ያልገባቸው የአገረው ምስለኔዎች ደግሞ የእነሱን መልዕክት ተግባራዊ ለማድረግ ለሆዳቸው ሲሉ ሌት ተቀን ይለፋሉ።
በመሐል ተቆርጦ የወደቀውንም የስርዓቱን ሰንሰለት (ደጃዝማች፣ ቀኛዝማች፣ ግራዝማች፣ ባራምባራስና ጭቃሹም) በምስለኔ አማካኝነት ቀስ በቀስ ለመቀጠል እየሞከሩ ነው።
አገረውም ነገ እኔ ሲሾም እሾማሃለሁ ብሎ ነፍጥ ቃል የገባለት እውነት መስሎለት ከብዙሃኑ ነጻ መውጣት ይልቅ ለአንድ ሰው ነጻነት ደፍደፍ ሲል ማየቱ ትልቅ ትዝብት ነው። “በሬ ሆይ ሳሩን እንጂ ገደሉን መች አየህ” እንዲሉ። ‘The world is not looking for servants, there are plenty of these, but for masters, men who form their purposes and then carry them out, let the consequences be what they may.” Woodrow Wilson
በ2008 ምርጫ ውድድር ላይ ፕሬዝደንት ኦባማ እና የቀድሞዋ ሰክረተሪ ኦፍ ስተት ወ/ሮ ኪልንተን በዲሞክራቶች እርስ በርስ ጥሎ ማለፍ ውድድር ላይ እንዲህ ስትል ቅዥች። “let’s take back our country” ዛሬ በአገራችንም ይህ አይነቱ ጎልቶ ይታያል። ከማን ነው ኪልንተን አገሯን የሚታስመልሰው? ኦባማ ማለት አሜርካዊ ዜጋ አይደለም ማለቷ ሳይሆን ስልጣን አይገባውም ሁለተኛ ዜጋ ነው ማለቷ ነው። 
ሁለተኛው አስገራሚ ነገር ደግሞ፣ ኦባማ በምርጫ ሲያሸንፍ ሪፓብሊካን በዘረኝነት እናሸንፋለን ብለው ስላመኑ፣ Tea Party (ሹልክ ብሎ ቅምስ ሻይ ፓርቲ) በማለት ካቋቋሙ በኋላ ኦባማን ሌት ተቀን በማጨናነቅ ሁለተኛ ምርጫ እንዳያሸንፍ ምክረው ነበር ነገር ግን ውርደታቸው ከፊቱ የባስ ሆኖ እርስ በርሳቸው ተፈረካከሱ። ኦባም አልቸው! “I have long enjoyed the friendship and companionship of Republicans because I am by instinct a teacher, and I would like to teach them something.” Woodrow Wilson 
በአገራችንም በአንድ በተክርስቲያንና መስጊድ ውስጥ ሌላ ራስ ገዝ ቲ ፓርቲ በማቋቋም ሌላውን ሕዝቡን ከፋፈላችሁ እያሉ፣ ራስቸው ግን ሕዝቡን ከፋፍለው ወደ ማይመለስበት መጥፎ አዝማሚያ እያመቁ ይገኛሉ። ይህ አንቀጽ 39 የሚሉት ነገር አገራችንን ሊያጠፋ ነው የሚሉት ነገር ግን የነርሱ እልክ ደግሞ ለባስ መጥፎ ክስተት እንደሚያመራ ማየት እንዳይችሉ አይናቸው ታውሮአል። እስቲ ሕዝብ በገዛ ክልሉ ቋንቋው፣ ወጉ፣ ሥርዓቱ፣ ባሕሉ፣ ልማዱ፣ ማንነቱ ተከብሮለት ሲኖር ነው ወይስ በፍረደ ገምድል ዳኛ ተግዝቶ ሲኖር ነው ዲሞክራሲ ሊባል የምንችለው? 
ለማንኛውም ድክመታችን መንግሥት ነው ተጠያቅ የሚሉ ነገር ግን የነበራቸውን የከፋ የመደብ ልዩነታቸውን ( ባሪያና ጌታ፣ ገባርና ጭሰኛ፣ ካፒታሊስቱና ወዛደሩ) ከነዘረኝነታቸው ጋር ደብቀው ይዘው ዛሬ አንድ ነገር ፈጥረን እናድራለን በማለት ያልሰለጠነ ጥሬ ፖለቲካቸውን (ለማለት እንኳን ያሳፍራል) አለምንም ፓርቲ ፕላን (platform) ባዶ ሜዳ ላይ ሲወራጩ ስናይ ወይ አለመታደል? እነዚያ ፖለቲካኞች የት ገቡና ነው እነዚህ ፕላን የሌላቸው፣ ባለው ላይ መጨመር ትተው ያለውን ለማንጥፋት የሚጥሩ ኋላቀር ፖለቲከኞች ከየት መጡ ትላለህ?
ዓላማቸው፡ ሌባ በመሰሉ እጅ ሲውድቅ ማየትን የመሰለ እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነገር የለም” ነው

     Give your opinion.