Discussion Forum

 ከግብጽ አሸባሪዎች ገቡ የሚለው ምን ያህል እውነት ነው? እውነት ከሆነስ በነዚህ ሰዎች ላይ መንግሥት ምን አይነት እርምጃ ወሰዴ?

የዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነው ከታች ያለው ጽሁፍና ቪዲዮ ነው። የተወሰደውም ከወ/ሮ/ት አሰቴር ደስታ ከምትባል ሰው ፌስቡክ ላይ የተቀነጨበ ከመሆኑም ሌላ ባጠቃላይ የስራቱ አቀንቃኞችና አዝማቾች ከሰሞኑ ቁጣ ጋር አያይዘው (እንጀራና ወጥ) በማድረግ የማሳመኛ መድሃኒት አድረገው በየቦታው በሶሻል ሚዲያ ላይ ስለጥፉ እናያለን።
Aster Desta
17 hrs ago·
ድሮ ና ዘንድሮ
የ ደሮ ጀግኖች
እነዚህ ሰዎች አፈሬን ይዘውብኝ እንዳይሄዱ ጫማቸውን አራግፋችሁ ባህሩን አሻግሯቸው። >>
ሃፄይውሃንስ
ዘንድሮ
# ሰልጣን ላግኝ እንጂ አደለም አባይ ግቡፅ ኢትዮፒያም ተግዛ
# ኢሃደግ የውረድ እንጂ iSIS ይግዛን
ታዲያ ምነው ዛሬ ??
https://youtu.be/zomNvgzZ9F4

ታዲያ ምን ያህል እውነት ነው? እውነት ከሆነስ በነዚህ ሰዎች ላይ መንግሥት ምን አይነት እርምጃ ወሰዴ?
አባይ የመገደቡ ጉዳይ ይሁን የአባይ ወንዝ ወደግብፅ የመጓዙ ጉዳይ ግብፅንና ኢትዮጲያን ለአያሌ ምዕተ አመታት ከብሉይ ኪዳን ጀምሮ ሲያዋጋና ሲያጣላ እንደቆዬ ለማንም ግልጽ ነው። አባይ በኢትዮጲያና በሱዳን፣ በኢትዮጲያና በግብጽ ብሎም በእንግሊዚና በኢትዮጲያ መሃከል ክፍተኛ ወጥረት አልፎ ተርፎም ይህ ወንዝ ለግብጻዊያን ደስታ ለኢትዮጲዊያን ደግሞ የዘላለም ጸጸትና ወርደት ሆኖ ይኖር እንደነበር የቅርብ ትዝታችን ነው። በአባይ ምክንያት አገራችን በርካታ ጥቅማ ጥቅሞችን ከአለም መንግስታት እንዳታገኝ ተደርጋ እንደቆየች እኛ ዘጎቿ ብቻ ሳንሆን አለምም ጭምር ያውቀዋል። ይህም ትኩሳት እያንዳንዱን ኢትዮጲያዊ ዜጋ እንደእሳት እንደሚለበልብ የስራቱ አዝማቾች በደንብ አድርገው ያውቁታል።
ስራቱ የራሱ የሆነ ደካማ ጎኖች እንዳሉት እናውቃለን። ዲሞኪራሲ፣ ነጻነት፣ ሰላም አለ ብሎ ለጎረበት አገሮች ጭምር ይዘምር እንጂ ዛሬ የኢትዮጲያ ህዝብ ካሉት በታች ከሞቱት በላይ ሆኖ አንገቱን አቀርቅሮ በፍሃት ይኖራል። የህዝቦች የነጻነት ቁጣ በጋየበት ቁጥር ሁሉ ስራቱና የስራቱ አዝማቾች ነገሮችን ካንዱ ወደሌላው በማሸጋገር የህዝቡን የልብ ትርታ በሚነካ መልኩ በማቀናበር ህዝቡ በቀደመው በታሪክ ቁርሾ ላይ ተጨማሪ ቂም እንዲይዝ በማድረግ የህዝቡን የነጻነት ጥያቄ ማደናቀፍ ወትሮም ልማዱ ነው።
እዚህ ላይ ማየት ያለብን፣ አቶ አንደርጋቸው ጽጌ የመን መድረሱን በመረጃቸው ስለደረሱበት የእንግሊዝ ዘጋ ቢሆንም ወዲያው ቁጥጥር ሰር አውለውታል። ቀጥሎ የሲዊድን ጋዜጤኛና ፎቶ አንሺዎች በኢትዮጲያ ኦጋዴን አካባቢ ድንበር አቋርጠው ገብተው የጋዜጤኝነት ስራቸውን ሳያስፈቅዱ ሲያካሂዱ በመድረሳቸው ወዲያ በቁጥጥር ስር አውለዋቸዋል። በኤርትራ የሰለጠኑ የኦጋዴን ነጻ አውጪ ገና ድንበሩን እንደተሻገሩና በመሻገርም ላይ እያሉ ነበር በቁጥጥር ስር ያዋሏቸው። ከሳውዲ አረቢያ ወደአዲአበባ የሱኒ ኢስልምናን ለማስተማር የመጡት ሸኮች ከአሸባርነት ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል ገና ከአውሮፕላን ጣቢያ ከተማውን እንደገቡ መልሰው እንደላካቸውም የቅርብ ትውስታችን ነው።
እዚህ ላይ የኔ ጥያቄ መንግስት 1ኛ እነዚህ ሰዎች ይህንን የተዛባ መልክት ይዘው ወደአገርራችን ሲገቡ እንዴት ዝም ብሎ አያቸው? እነዚህ ሰዎች ወንጀለኞች ወይም አገር ለማጥፋት ተልኮ እንዳላቸው እየታወቀ እንዴት በሚዲያ ላይ ስለነዚህ ሰዎች በግልጽ ቀርቦ ማስጠንቀቂያ አልተሰጠም? እነዚህ ሰዎች የአንድ አገርን ሉዓላዊነትን ለማጥፋት ቀደም ሲል ከተጠቀሱት ከነ ኦጋዴን ነጻ አውጪ ድርጅት፣ ከሌሎችም አሸባሪ ናቸው ከተባሉት እንደማይተናነሱ እያወቁ እንዴት ባገራችን እስካሁን አቆይቷቸው ነው በሬቻ በዓል ሳቢያ አሁን ሊያወጡት ቻሉ የሚሉትን መጠየቅ አስፈላጊ ይመስለኛል።
በ2ኛ ደረጃ ቀደም ሲል በርከት ያሉ ህዝብ ለማሳመን በሚል ምክንያት ወያኔ የሚካሂዳቸው ሴራዎች እንዳሉ ተምረናል። ተቃዋሚ ሰላማዊ ሰልፍ ሲያደርግ መንግሥት የራሱን ደግሞ አሰልፎና በፖሊስ አስገድዶ ሌላ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያወጣ፤ ተቃዋሚዎች ለምርጫ ቅስቀሳ በሚወጡበት ወቅት፣ የመንግስት ካድሬዎች ተቃዋሚዎች እቦታው ሳይደርሱ ቀድመው የራሳቸው የሆነ ስብሰባ አዘጋጅተው እንደሚያቆዩ፣ አዲስ ተቃዋሚ ፓርቲ ለማቋቋም ቅስቀሳ ሲደረግ ከሰሙ ለጽ/ቤት የሚሆን ቦታ እንዳይከራይላቸው በማድረግና በመሳሰሉት ነገሮች ሳቦታጅ ሲያደርግ እንደነበር በደንብ እናውቃለን። ታዲያ እነዚህ ግብጻዊያን ናቸው የተባለት ሰዎች በመንግሥት ያልተቀናበሩና በግብጽ ሰለመቀናበራቸው ምን ማረጋገጫ አለን? ከሆኑስ ለምን አልታሰሩም? ከታሰሩስ የት ነው የታሰሩት? አሁን ሰሞኑን ከግብጽና ከሱዳን ጋር ስምምነት አደርጉ ያለውስ ይሄው መንግሥት አይደለም ወይ? የነዚህ የወንጀለኞች ፓስፖርት፣ ሌላም መታወቂያ ከነሰነዳቸው ጋር ተያይዞ ለምን ለህዝብ ይፋ አልሆነም? የግብጽ መንግሥት በዚህ በአገር ጉዳይ ጣልቃ ከገባ የአገር ል ዓላዊነት ድርድር አይቀርብምና ምን አይነት ቁርጥ ያለ እርምጃ ተወሰደ? ወይስ ይህንን በጣም አንገብጋቢ የሆነ የአገር ጉዳይ ለፖለቲካ ፋይዳ ሲሉ ቀምረውታል? የቱ ነው እውነት?

ግን ክዚህ ሁሉ የቱ ይቀላል? ዲሞክራሲን ራሴ እንዳወጅኳት ራሴ ብቻዬን እበላላሁ በማለት አገርን ማወደም፣ ግብጽን ማማት፣ ኤርትራን ማጋየት ብሎም በኪሳራ ላይ ኪሳራ ወይስ ሁሉንም ዜጋ ሰብስቦ ለአገራችን እርቅን ማወረድ? የወያኔ የፖሊሲው አቅጣጫ ፓርማታ ላይ ደርሷል። ወራጁ አልወርድም መልሰህ አዙረህ አምጣኝ ይቻላል? ወይስ በአዲስ መንፈስ ህዝብ የፈለገውን ከመረጠ በኋላ አገርን ከጥቃት ማዳን? ችግሩ ህወሃት ድንጋይ የሆነ ግትርነት እንዳለውና ለተስታም ጎበዝ እንደሆነ እንሰማለን ታዲያ ለተስታ የሚሆን ራስ የለም ሁሉም ወደሰባዎቹ እየደረሱ ናቸው። ይህ ሁሉ መሯሯጥ በፍጹም መፍትሄ ሊሆን አይችልም።
ስለዚህ ይህ ጉዳይ በጣም አጠያያቂና አነጋጋሪ ስለሆነ እስቲ አድማጩ ምን ይላል እላለሁ አገር ማዳን መፍትሄው ምንድነው?

     Give your opinion.