Discussion Forum

 በ2026 ዓለም ደህና ሰንብች ለማለት የመጀመሪያዎቹ ላይመለሱ ወደማርስ ተጓዦች ዝግጅት ላይ ናቸው።

 

በ2026 ዓለም ደህና ሰንብች ለማለት የመጀመሪያዎቹ ላይመለሱ ወደማርስ ተጓዦች ዝግጅት ላይ ናቸው።

ከዚህ ቀደም ሁለተኛ ላለመለስ ወደማርስ ተጓዦችን አስመልክቶ (Cost to Cost am radio) ባቀረበው ዘገባ ላይ ዝርዝር ሁኔታዎችን ሰምቼ ነበር። ዛሬ ደግሞ በሲኤን ኤን ላይ ያንኑን የሚያተኩር ዜና አቅርበዋል። በዚህ ዜና ላይ እንደተናገሩት ለመጀመሪያዎቹ ተጓዦች ዝግጅቱ ቀጥሎአል ሲሉ የጉዞው አሰተባባሪ ዋና አዛዥ ላስ ላንድስዶርፕ ተናግረዋል። ስለዝግጅቱ ሲናገሩ 200000 በምዝገባው ብካተቱም እኛ ግን የምንወስደው በየሁለት አመቱ አራት ሰው ብቻ ነው። እነዚህ ሰዎች ግን ሁለተኛ ወደምድር አይመለሱም። ስለአወሳሰዱ ለመመረጥ ቅድሚያ ይሰጠዋል የተባለው መለኪያ በሙያቸው መሃንዲስና የጤና ባለሞያዎች ሲሆኑ ዋናውና ቁልፉ እዚያ ለመኖር የሚያስችለው መተባበር ነው። የመጀመሪያው ጉዞ ወጪ የተመደበው በጀት 6ቢሊዮን ዶላር ነው። ማለት በግምት አንድ ሰው ወደ 2ቢሊየን ዶላር ይከፍላል ማለት ነው።  

በአንድ ወቅት ከላይ ከተጠቀሰው ሬድዮ አዘጋጆች ጋር በደረጉት ቃለምልልስ የሚከተውለውን በማለት መልስ ሰጥተዋል።

1 ማርስ (ቀዩን ፕላነት) ስትሄዱ ሃይማኖት፣ ጋብቻና፣ መንግሥት ይኖራል ወይ ተብለው ሲጠየቁ፡ - የሚከተለውን መልሰዋል። ማርስ ምንም አይነት ሃይማኖት፣ መንግስት እና ጋብቻ አይኖርም። በተለይ በማርስ ምንም አይነት የግብረ ሰጋ ግንኙነት አይደረግም።

  1. ከምድር የሚጓጓዘው መኖ ቢያልቅ ወይም የመጓጓዣ ችግር ቢኖን ምን ትሆናላችሁ ተብለው ሲጠየቁ፡ - በማርስ በቂ አትክልትና ፍራፍሬ ማምረት እንችላለን፤ በዚያ ብቻ ራሳችንን ለበርካት ጊዜያት መመገብ እንችላለን ብለዋል።

     Give your opinion.