የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በአዲስ መልክ ያደራጁትን ካቢኔ በሙሉ ድምፅ አፀደቀ

7-19-2017

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በአዲስ መልክ ያደራጁትን ካቢኔ አዳዲስ አባላት በሙሉ ድምፅ አፀደቀ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ቀደም ሲል የነበረው በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማእረግ በክላስተር የማስፈፀም  እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ የሚሉ ቦታዎች ሙሉ በሙሉ መቅረታቸውን አስታውቀዋል። እያንዳንዱ የካቢኒ ሚኒስትር ስራውን በውጤታማነት እንዲያከናውን የሚያደርግ ስራም ተጀምሯል።

የካቢኔ ሚኒስትርነት የተወሰኑት ባስመዘገቡት ውጤት ተመዝነው በቦታቸው እንዲቀጥሉ የተወሰኑት ደግሞ እንዲሸጋሸጉ እና በአብዛኛው ደግሞ አዳዲስ የካቢኔ ሚኒስትር አባላት እንዲካተቱ ተደርጓል ነው ያሉት።

የካቢኒ ሚኒሰትሮቹ ዋና መመዘኛም ውጤታማነት እና ለህዝብ ውግንና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠትን ያተኮረ ሆኖ፥ በቀጣይነትም በውጤት ተመዝነው ማስተካከያዎች እንደሚደረጉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል። 

"አዳዲስ ሚኒስትሮችም ምርጫ በአብዛኛው የእድገት ደረጃችን የሚጠይቀው ዝንባሌ፣ አውቀት እና ክህሎት ያላቸው፣ ቀድሞ በሰሩባቸው የከፍተኛ ትምህርት እና የምርምር ተቋማት እንዲሁም በሙያቸው፣ በተሰማሩበት መስክ ውጤታማ የነበሩ፣ በመልካም ስነ ምግባራቸው፣ በስራ ትጋትና ታታሪነታቸው የሚታወቁትን በማፈላለግ የተፈፀመ ነው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በካቢኔ ውስጥ ባሉበት ይቀጥላሉ ያሏቸው አባላት

 1. አቶ ደመቀ መኮንን፦ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
 2. አቶ ሲራጅ ፈጌሳ፦የመከላከያ ሚኒስትር
 3. አቶ ካሳ ተክለብርሃን፦የፌደራል ጉዳዮችና አርብቶ አደር አካባቢ ልማት ሚኒስትር
 4. ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፦የመገናኛና ኢንፎርሜሽን  ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
 5. አቶ አህመድ አብተው፦የኢንዱስትሪ ሚኒስትር
 6. አቶ አብዱልፈታህ አብዱላሂ፦የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
 7. ዶክተር ይናገር ደሴ፦የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር
 8. አቶ ጌታቸው አምባዬ፦የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
 9. አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ፦ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትርናቸው።

አዲስ የካቢኒ አባላትም፦

 1. ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
 2. አቶ ታገሰ ጫፎ፦ የፐብሊክ ሰርቪስ እና ሰው ሀብት ልማት ሚኒስትር
 3. ዶክተር አብረሃም ተከስተ፦ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር
 4. ዶክተር በቀለ ቡላዶ፦ የንግድ ሚኒስትር
 5. ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ፦ የእንሰሳትና የዓሳ ሀብት ልማት ሚኒስትር
 6. ዶክተር ኢያሱ አብረሃ፦ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትር
 7. ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ፦ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
 8. አቶ አህመድ ሺዴ፦ የትራንስፖርት ሚኒስትር
 9. ዶክተር አምባቸው መኮንን፦ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትር
 10. ኢንጂነር አይሻ መሀመድ፦ የኮንስትራክሽን ሚኒስትር
 11. ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ፦የውሃ፣ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስትር
 12. አቶ ሞቱማ መቃሳ፦ የማዕድን፣ የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስትር
 13. ዶክተር ገመዶ ዳሌ፦ የአካባቢ ደን ልማት እና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስትር
 14. ዶክተራው ሽፈራው ተክለማርያም፦ የትምህርት ሚኒስትር
 15. ፕሮፌሰር ይፍሩ ብርሃነ፦ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር
 16. ዶክተር ግርማ አመንቴ፦ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትር
 17. ዶክተር ሂሩት ወልደማርያም፦ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር
 18. ወይዘሮ ደሚቱ ሃምቢሳ፦ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስትር
 19. አቶ ርስቱ ይርዳው፦ የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስትር
 20. አቶ ከበደ ጫኔ፦ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሃላፊ ሚኒስትር
 21. ዶክተር ነገሪ ሌንጮ፦ የመንግስት ኮሙዩንኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሀላፊ ሚኒስትር ናቸው።

ምክር ቤቱም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረቡትን የካቢኒ አባላት በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በተጨማሪም ለተለያዩ ኃላፊዎች በሚኒስትር ደረጃ ሹመት ሰጥተዋል። በዚህም መሰረት፦ 

 1. አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ፡- በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታጉዳዮች ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ
 2. አቶ አብዱልአዚዝ መሐመድ ፡- በየዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታማስተባበሪያ ማዕከል የፖለቲካ ፖርቲዎችና ሲቪክ ማህበራት ጉዳዮችአስተባባሪ

  3. አቶ ተፈራ ደርበው ፡- በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ

  4. ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሔር፡- በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል የከተማ ዘርፍ አስተባባሪ በማድረግ የሚኒስትር ማዕረግ ሹመት መስጠታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አስታውቋል::

     Give your opinion.