ዲሞኪራሲ በጊዚያዊ አዋጅ የሚቆም ወቅታዊ ፈሳሽ ወንዝ አይደለም።

7-19-2017

ዲሞኪራሲ በጊዚያዊ አዋጅ የሚቆም ወቅታዊ ፈሳሽ ወንዝ አይደለም።
ህወሃት ስልጣን ከመያዙ በፊት በጫካ ውስጥ ሳለ የገዛ ህዝቡን በሃውዜ ደርግ ገደለ ለማስባል አስጨፈጨፈ። ይህ ገዳይ፣ ት/ቤቶችን፣ ጤና ጣቢያዎችንና ድልድዮችን ስሰብር እዚህ ድረስ የመጣው የሽፍታው ቡድን፣ ለተዘጋጀለት የግል ፍላጎት አይመቸኝም በማለት ከራሱ ጋር በትግል ሜዳ የቆየውን ኦነግንና ሌሎችንም ጠመንጃቸውን በማስፈታት ነበር ኢትዮጲያን በትግራይ ቅኝ አገዛዝ ስር የጣለው። ፤ከዚህም የተነሳ ነው የትግራይ ክልል ሌላውን የኢትዮጲያ ክልል አስገብሮና ዘርፎ ትግራይ ክልል መሬቷ መሸከም ከምትችለው በላይ ሃብት የጫኑባት። ህወሃት በቀደምት የስልጣን ዘመናቱ ከ1983-85) አቶ ልዴቱ አያሌው እንዳሉት “ኢሃደግ ሲጀምር ለማልቲ ፓርቲ ስስተም የተዘጋጀ ሆኖ አሁን ግን ለማልቲ ፓርቲ ስራዓት በሩን የዘጋ ሆኖ እናያለን” እንዳሉት ዛሬ ያን ያህል ደም ፈሦ እንኳን ከማታለል አልወጣም። ወያኔዎች ከፊት መምራት ሲያቅታቸው በጓሮ በር እየገቡ መስራት ጀምረዋል። ይልቅ በጓሮ ይቅርባችሁ የዘረፋችሁት ሃብት ይበቃል እንላለን።
የቀድሞው ጠ/ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ከመሞቱ በፊት ያሁኑን ጠ/ሚኒስተር ሃ/ማሪያም ደሳለኝን አለምን ለማጭበርበር እንዲያመቸው ም/ጠ/ሚኒስቴር አድርጎ (ከወላይታ ከሾምኩ ይህ መንግሥት ዲሞክራሲያዊ ነው ለማሰኘት ይመቸኛል በሚል) መሾሙ ይታወቃል። ወጣም ወረደ ጠ/ሚኒስተር ሃ/ማሪያም ደሳለኝ የራሳቸው የሆነ ራዕይ ስለሌለኝ የመለስን ራዕይ እንደሆን በሚገባ አጥንቻለሁ እንደሱም መናገርና ኮፒ ማድረግ ተምርያለሁ ብሎ በገቡት ቃል መሰረት የሚቀለውን የህዝብ ጥያቄ መመለስ ትተው ለራሳቸው፣ ለህዝባቸውና፣ ብሎም ለአገራቸው ራዕይ አጥተው ለሰው ራዕይ ሲሉ በጊዜያዊ አዋጅ፣ በጥልቀት እድሳት በሚል ውሃ ቅዳ ወሃ መልስ ውስጥ ህዝቡን ከማሰቃየትም አልፎ፣ በተባበሩት መንግሥታት ስብሰባ ላይ ሜድያ(ፌስቡክ፣ ቱዊተር) ከአለም ላይ ይወገድ እስከማለት በመድረስ የዓለም መሳቂያና መቀለጃ ሆነዋል።
የህዝቡ ጥያቄ ቀላልና አጭር ነው። 1. መጀመሪያ የጎሳ ፖለቲካ የጥላቻ ፖለቲካ ነውና ሰዎች በዘሮቻቸው ሳይሆን ባላቸው እውቀትና ችሎት በሚያቀርቡት ሃሳብ መሰረት ያደረገ ህገመንግሥት እንዲስተካከል ይደረግ። 2. ይህ ተያይዛችሁ የምትለጣጠፉበት እከከኝ ልከክህን የወደቀ ማርክሥስት ሌኒንስት ፓርቲ ዲስፒሊን ፖለቲካ ትታችሁ ግልጽ የሆነ በህዝብ ፍላጎት ላይ መሰረት ያደረገ ህዝባዊ ምርጫ ይካሄድ፣ 3. አዲስ በጥልቀት መታደስ በሚል ግለሰቦችን ከቦታ ቦታ መቀያየሩ ጉልቻ ቢቀያየር ወጥ አያጣፍጥም ያልነውን እውን ያደርገዋልና አቁሙ። 4. አንዳችም ከኢሃደግ (ከመለስ) ዕላማ አልወጣም ስለዚህም ጠ/ሚኒስትሩ ራዕይ ከሌለቸው ለሌላ ራዕይ ላለው ሰው ወይም ፖርቲ ለምን ቦታውን አይለቁም? እዚህ ላይ በሰውነት ደረጃ ጠ/ሚኒስቲሩ ጥሩ ሰው ሊሆኑ ይችላሉ ነገር ግን በፖለቲካው ረገድ የዘመኑ ፖለቲካ ከርሳቸው ቀድሞአልና ባልሆነ ቦታ ገብተዋል እላለሁ።
ለዲሞክራሲ መዳበርና በአገሪቷ ለሚመጣው ዲሞክራሲያዊ የፖለቲካ ለውጥ ይሆናሉ ተብለው የተመረጡት መባረር ያልቀርላቸው የአቶ ሺፈራው ሽጉጤ (ፀረ-ዲሞክራሲ) ለዲሞክራሲ መዳበር መድረክ ላይ መሪ ሆነው መመረጣቸው ብቻ ጠ/ሚንስትሩ ለህዝብ ጥያቄ ምን ያህል ትክረት እንዳልሰጡና ንቀታቸውን በግልጽ አሳይቷል። ከደቡብ ክልል ማን ለቦታው ይመቻል ተብሎ ከክልሉ በህዝብ ምርጫ፣ ጥቆማና ምዘና መሆን ሲገባ በፍርደግምድልነትና በማን አልብኝነት ማን በአዲስ አበባ የሚኖር የደቡብ ሰው አለ ብሎ ከኢሃደግ ካድሬነት እርከን ላይ ያለውን ደቡብን ይወካላል፣ ሰሜንን ይወክላል፣ ብሎ የማስቀመጡ ጉዳይ ትግሬዎችን ከህዝብ ፊት እንዴት እናሽሽ ለማለት የተደረገ ድርጊት እንጂ እውነተኛ እውነታ አለመሆኑን በደንብ እናውቀዋለን። ይህ አይነቱ ድብብቆሽ የሚያስከትለው መዘዝ ቀላል አድርገው አስበው እንደሆን ጠ/ሚኒስትሩ ተሳስተዋል። ህዝቡ ይህ መንግሥት የሚወገድ እንጂ የሚጠገን አይደለም ሲል በተጸራሪው በማጠናከሪያነት ህዝቡን በደህንነት ስጋት ላይ ጥሎ ዲሞክራሲን የማፈኑ ጉዳይ በፍጹም የምዋጥ ነገር አይደለም።
በደቡብ ክልልም ከላይ ያሉት እንዳደረጉ ሁሉ እኛም በጥልቀት እየታደስን ነው ለማለት ሙሰኞችን እንደሹጉጥ በጣታቸው ማሽከርከር ጀምረዋል። እሲቲ ምን አድርገው ነው ለሹመት የሚዘጋጁት? ለገዛ ቤታቸው በር ላይ አስፓልት ስላሰሩ? የሰው ምስት ስለደፈሩ? ያልሆነ ስም ሰጠተው ነጹሃን ዘጎችን ለወይኒ ስላበቁ? 2,392,886 የጋሞ ብሄረሰብ የለም አስብለው መጽሃፍ ሳልጻፉ? ለልማት ተብሎ የሚላክ በጀት ስለተቀራመቱ?
ህዝብ ሞኝ አይደለም ሁሉንም ያውቃል፣ የዚህ መንግሥት ተላላኪ ካድሬዎችና የኢሃደግ ፖርቲ መሪዎች ለካድሬዎቻችሁ የምትከፍሏትንና እያከፈላችሁ ያለውን የህዝብ ገንዝብ በእዳ ራሳችሁ እንደምትከፍሉ ካሁኑኑ ልታውቁ ይገባል። ለአንድ ፓርቲ ካድሬ ብቻ ከመንግስት ካዚና ገንዘብ ወጪ ሊሆን አይችልም። ዲሞክራሲ እግ/ር ሲፈጥረን የቸረን ስጦታ ስለሆነ የማይቀርላችሁን የህዝብ ነጻነት ለባለቱ ለህዝቡ የማስገባቱ ጉዳይ የማያጠያይቅ ፍቱን መድሃኒት ነው። ዲሞኪራሲ በጊዚያዊ አዋጅ የሚቆም ወቅታዊ ፈሳሽ ወንዝ አይደለም።

 
 

     Give your opinion.