የተደረገው ሽግሽግ የዲሞኪራሲ ውጤት ቢሆን ምነኛ አስደሳች ነበር?

12-14-2016

የተደረገው ሽግሽግ የዲሞኪራሲ ውጤት ቢሆን ምነኛ አስደሳች ነበር?

የማይቋርጥ ዕድገትና ዲሞክራሲን ለዘለአለም የሚቆይ እውነታ በሆነ ነበር። ሆኖም ግን የአንድ ፓርቲ የበላይነትን ብቻ የሚያንጸባርቅ በመሆኑ የዲሞኪራሲ ህሊውና እጅግ አጠያያቂ ሆኖአል። የተማረ ህብረተሰብ አስፈላጊና ውጤታማም ነው ሆኖም የተማረን ሰው መተካካት ህዝቡ ለዲሞኪራሲ የሚያደርገውን ጥያቄ ሊገታው አይችልም። ወጣም ወረደ ተመራጮቹ የአንድ ፓርቲ ወጥ ምልምል አባል ስለሆኑ ለፓርቲያቸው ይገዛሉ፣ ይህ እስከሆነ ድረስ የብዙሃኑ ጥያቄ መልስ ያገኘ ሳይሆን የአንድ ፓርቲ የበላይነትን በጠንካራ መሰረት ላይ ለመገንባት የተደረገ መሙለጭለጭ ነው። የህዝብ ጥያቄ የዲሞክራሲ ጥያቄ ነው። ወያኔ ከኢሃደግ ሌላ አንድም ፓርቲ በአገሪቱ እንዳይለመልም ባቀደው መሰረት ላይ የተደረገው ሽግሽግ እየተንኮታኮተ ያለውን የኢሃደግን ነፍስ የለሽ መንግሥት ከሞት የሚያድነው አይደለም። ኢሃደግ መወገድ ያለበት አሊያም በአግሪቱ እንደአንድ ፓርቲ ሊወዳደር የሚችል ፓርቲ እንጂ መጠገን ያለበት አምባገነን አይደለም።

ከዚህ ጋር አያይዘን የሚከተለውን የሹመት ዝርዝር ሁኔታ እንደሚከተለው ከሴፒ ኢዲ ኤም(SPEDM) ያገኘነውን እንደሚከተለው አስቀምጠናል።

የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦች ህዝቦች ክልል ምክር ቤት በአስቸኳይ ጉባኤ,,,, የመስትዳድር ምክር ቤት አባላት እና ሌሎች አዳዲስ ሹመት አጽድቋል,,, እንረዲሁም ከዚህ ቀደም በምክትል ር/መስትዳደር ማእረግ የክላስተር የነበሩ ሹመቶች እንዲቀሩ ተደርጓል
አዳዲስ ካቢኔ የተሾሙ አመራሮች
1. ዶ/ር አብርሃም አላኖ /PhD/ የጤና ቢሮ ኃላፊ
2. ዶ/ር እሸቱ ከበደ /PhD/ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ
3. ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ/PhD/ የውሃና መስኖ ልማት ቢሮ ኃላፊ
4. ዶ/ር አክመል መሐመድ/PhD/ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ
5. ዶ/ር ሀሚድ ጀማል/PhD/ እንስሳትና አሣ ሀብት ቢሮ ኃላፊ
6. ዶ/ር ጌትነት በጋሻው/PhD/ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ
7. ወ/ት ትዝታ ፍቃዱ የፍትህ ቢሮ ኃላፊ
8. አቶ ሰለሞን ኃይሉ የመንግሥት ኮሚንከሸን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ
9. አቶ ንጉሤ አስረስ የገቢዎች ባለሥልጣን ዋና ዳይረክተር ሆነው የመስተዳደር ምክር ቤት አባል እንዲሆኑ ተሸመዋል፡፡

     Give your opinion.