የትግሬ የበላይነት ያጠለለው የዘር ጭጋግ የጫረው የማያቆም የርስበርስ ጦርነትና ግጭት

1-3-2017

የትግሬ የበላይነት ያጠለለው የዘር ጭጋግ የጫረው የማያቆም የርስበርስ ጦርነትና ግጭት
መነሻው ራስ ወዳድነት ነው። “የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ” ይባል የለ? ከዚህ በታች ባሉት ላይ ይህ ነው የማይባል ዜናዎችና መጋለጦች በየድህሬ ገጾች ላይ በደረደርም የሙስናው መነሻ የሆነው የትግሬው ሃወሃት ቡድን እኔ ከተነካሁ ወየውልህ የተባለው የሃ/ማሪያም ደሳለኝ መንግስት ስርነቀል የሙስና ለውጥ ማካሄድ በፍጹም አልቻለም። ቢኖርም በሌለው ገና ታዳጊ ሞሳኙ ላይ የሚወሰድ እርምጃ እንጂ በእንደነ አርከቤ እቁባይ፣ በንደነ አባይ ጸሃይ፣ በንደነ አባይ ወልዱ፣ በነደነ ስብሃት ነጋ፣ በእንደነ አራያ ዘርሁን፣ በንደነአዘብ መስፍን አይደለም። ምክንያቱም እኛ ትግሬዎች ለናንተ እንደክርስቶስ ሞተናል ስለዚህ ክፍያ እንፈልጋለን በማለት በስሜ ሰማዕታት የገነዟቸው ስለሆነ ፍታቱም ሆነ ልቅሶው ብሎም ቀብሩ የሚካሄደው በነሱ ብቻ ነው። ታዲያሳ? ይህ ከታች ያለው ድርጅት ከየት በመጣ ገንዘብ ነው የተቋቋመው?
Messebo Building Materials Production P.L.C, Mesfin Industrial Engineering Ezana Mining Development P.L.C. (EMD) Saba Dimensional Stones P.L.C. (SDS) SUR Construction Plc. Express Transit Service P.L.C. (EXTRAN) Addis Pharmaceutical Factory (APF) Guna Trading House P.L.C. Hiwot Agricultural mechanization P.L.C Sheba Tannery P.L.C. Almeda Textile Factory P.L.C. Experience Ethiopia Travel (EET) Trans Ethiopia P.L.C.
ስንት ያልተባለ ነገር አለ?
 በምርጫ ማግሥት: ሕገወጥ መሬት ባለይዞታዎች ሕጋዊ ካርታ ተሰጣቸው – የሕወሃት ሰዎች ከ97 ጀምሮ በሕገ ወጥነት፥ ተንኮልና ነጠቃ የያዟቸውን እንደሚጨምር ታውቋል፤ እሪ በይ ኢትዮጵያ!
 በዕጦቶችና የሥልጣን ብልግና የተፈጠረው የኢትዮጵያ ምሬቶች የዛሬው ሥዕልና የነገው ሥጋት*
 መንግሥታዊ አስተዳደር በሃገራችን አለመኖር! በአዲስ አበባ የኦዲት ችግር ተስተውሎባቸው እንዲያስተካክሉ ከተነገራቸው 125 መስሪያ ቤቶች ምላሽ የሰጡት 9 ብቻ መሆናቸው ተነገረ!
 በመንግሥታዊ ተቋማት በስድስት ዓመታት ብቻ ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ገንዘብ በሕገወጥ ግዥ ተፈጽሟል፤ በተለይ አንድቢሊዮን ብሩ በዩኒቨርሲቲዎች ብቻ የተፈጸመ ሙስና ነው
 ከዚህም ጋር በማያያዝ በአርባምንጭ ሆስፒታል ስለተካሄደው የገንዘብ ዝርፊያ ከዚህ ቀደም በሰበር ዜናነት ገልጸን መፍትሄ እየተገኘለት ያለ ቢሆንም አሁንም ቢሆን ሙሰኞቹ ሽንጣቸውን ገትረው ከውንጀል ለመዳን የማይፈንቅሉት ድንጋይ እንደሌለ ሆኖ ሳለ አሁንም ቢሆን የአርባምንጭ ሆስፒታል በቂ የህክምና መሳሪያዎችን ሊያገኝ አለመቻሉ በስራውና በታካሚው ህዝብ ላይ ከባድ ጉዳት እያስከተለ መሆኑን ምንጮቻችን እየገልጹ ነው።
ሰሞኑን እንኳን ከልማት ባንክ ጋር በተያያዘ ለግብርና እንቬስትመንት ተብሎ ከተሰጠው 4.3ቢሊዮን የገንዘብ ብድር ውስጥ 668 ሚሊዮን ብር የት እንደገባ በላመታወቁ የባንኩ ፕሬዚደንት ከስራው ሲባረር ገንዘቡን በሃልፊነት ሳይጠየቅ በሰላም ወደቤቱ ይዞ መግባት የተዘረፈው ገንዘብ በስሜ ብድር ሆኖ ነገር ግን እዳው ለመጪው ትውልድና ለአገሪቷ ሆኖ የመቅረቱ፣ ለአስር ስኳር ፋብርካ የተመደበው 77ቢሊዮን ብር የት እንደገባ አለመታወቅና ተጠያቂ መጥፋቱ፣ ሙስናንና መልካም አስተዳደር ለማስፈን በሚል አዲስ መዋቅር መዘርጋት ከተጀመረ በኋላ እንኳን በአያሌ ካሚዮኖች የተጫነው ብረታብረት ደብዛው መጥፋት፣ በርካታ ገንዘቦች ከባንኮች በየቀኑ የመዘረፍ ጎልቶ ይገኙበታል። ታዲያ ይህን እዳ ወደፊት ተሸካሚ የሆነው ወጣት እሃደግ ፓርቲ ብሎ በሻበበው የአህያ ቆዳ ሁሌ ጅብ ሲጮ እየላላ በይሉኝታ እንደሚዳቋ ሌት ተቀን እያሰጋ ይኖራል። እዳው እንደሆን መከፈሉ አይቀረ ነው። አሊያም ወለዱ አይጣል ነው። ታዲያ የኢሃደግ ወጣቶች ሊግ የሚለው የሃሰት መሰረት የሌለው በጥቂት ሰዎች የሚመራው ድርጅት እስከመቼ እያታለለ ይኖራል?
የዲሞክራሲ ሙስና
የገንዘብና የመሬት ሙስናውስ ይቅር እንደው የሰው ልጅ መብትም በሙስና መረቅ ተፈትፍቶ እንዲሁ ቀልጦ ይቅር?
አቶ ሺፈራው ሽጉጤ ከስልጣን እንደሚባረር ብንናገርም ማንም ያመነ አልነበረም። አቶ ሺፈራው እንደማስቲካ ተመጥጦ ተወርውሮአል። ወጣም ወረደ አቶ ሺፈራውን ከስልጣን ያባረረው የሾመው ህወሃት እንጂ ሃ/ማሪያም ደሳለኝ አይደለም። ሃ/ማሪያም አቶ ሺፈራውን ላለማስቀየምና ለማጽናናት ሲል የዲሞኪራሲ አማላጅ ሞግዚት አድርጎ ሾሞታል። ለአቶ ሃ/ማርያም ዋናውና ቀዳሚው ትኩረት አቶ ሺፈራው ሽጉጤ አይደለም ነገር ኢየሃደግን ፓርቲ በስልጣን ላይ የማቆየቱ አደራ ከመለስ የተሰጠው መሆኑ ብቻ እንጂ። ዲሞክራሲ እንዲያብብ ሃ/ማሪያም ስልጣን ከያዘባት ቀን ጀምሮ አስቦም ተክዞም አይውቅም። ኢትዮጲያ ውስጥ ዲሞክራሲ ሰፈነ አልሰፈነ ለአቶ ሃ/ማርያም ደንታውም አይደለም። ለዚህም ነበር አቶ ሃ/ማሪያም ደሳለኝ የቅርብ ጓደኛውንና ዲሞክራሲን ከተጠማው ከሲዳማ ህዝብ ተወልዶ ያደገውን፣ ነገር ግን ከራስ ወዳድነቱ የተነሳ ዲሞክራሲን ለመግደል የቆረጠውን አቶ ሺፈራው ሽጐጤን ለዲሞክራሲ ምግዚት አድርጎ የሾመው። ኢትዮጲያ ትልቁ መርዶዋ ዲሞክራሲ ሊመጣ የሚችል ህልም አለመሆኑ ብቻ ነው። ስለዚህ ዲሞክራሲም እንደሙስናው የሞተ ነገር ነው።

ከትግራይ የሃብት ማካበት ልምድ በመውሰድ ወደወላይታ አቅጣጫውን የቀየረው የሃብት አዙሪት
ሰሞኑን ነበር የጠ/ሚኒስትር ሃ/ማሪያም ባለቤት ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ ወላይታ ውስጥ የልማት ማህበርን ለመጠናከር ደፋ ቀና ማለት የጀመረችው። ወይ አቶ ሃ/ማሪያም? አሁን ማን ይሙት ወላይታ ውስጥ ምን አይነት ልማት አለ? ይልቅ በሰፈራ መልክ ወጣቱን ከወላይታ አንስተህ ሌላ ቦታ ወስደህ ማስፈር ካልችልክ የወላይታ ህዝብ ቁጥር ከመሬቱ ስፋት ስለሚበልጥ በልማት መልስ የሚያገኝ ሳይሆን ሌላ ሰፋፊ መሬት ወዳለበት ወስደህ በማስፈር ብቻ መልስ ታገናለህ። ለዚህም ማስፈርም ይሁን ሌለላ ጉዳይ ልማቱን እኩል ለሁሉም ስታዳርስ ብቻ ነው። ወላይታን ከትግራይ የሚለየው በደጋማው በዳሞት ተራራ ላይና አካባቢ መሆኑ ብቻ እንጂ ሌላ ምንም ልዩነት የለም። እዚህ ላይ የወላይታ ህዝብ በነ አስተያየት መቀየም የለበትም ባይ ነኝ ምክንያቱም የጋሞ ጎፋ ህዝብ እንደጠቃሚነቱ በወላይታ ህዝብ አልተከበረም። ለወላይታ ህዝብ እድገቱም ሆነ ህይወቱ ቁልፉ ሚና ተጫዋቹ የጋሞ ጎፋ ምድር ነው። የወላይታ ነፍሱ ጋሞ ጎፋ ነው። እኛ ባንኖር ኖሮ ወላይታ ይኖራል ብዬ በእውነት አላምንም። የኛ የቆርጋ መሬት፣ የዋጅፎ፣ የም/አባያ፣ የፋራጎሳ፣ የጫኖ፣ የአርባምንጭ፣ የሼለ፣ የዳና፣ የቁጫ፣ የጎፋ መሬት ከለውጡ ጋር ተያይዞ ባስገኘው ድል ውርስና ሃብት ሆኖ በናንተ እጅ ቀርቷል። እኛም ለናንተ ጨካኝ አልነበርንም። ግን እናንተ ለኛ እጅግ በጣም ጨካኝን አረመነያዊ አስተሳሰብ አላችሁ። ሚኒልክ ከናንተ ጋር በሚዋጋበት ወቅት የጋሞ ጎፋ ህዝብ ከናንተ ጋር እኩል ክጎናችሁ ቆሞ እንዳልተዋጋ ታርኩን ሁሉ ማስታወስ አቃታችሁ። መሬታችንን፣ ባህላችንን፣ ቅርሳችንን፣ አባያችንን ወረሳችሁ አሁንም ምኞታችሁ በዚያ አላበቃም።የመጣችሁበትን ታርክ በመርሳት ራሳችሁን ብቻ ከፍ ከፍ ማድረግ ጀመራችሁ። የአርባምንጭ ዩንቬርሲቲ ወደወላይታ ካልዞረ ብላችሁም ታግላችሁ ነበር፣ የአርባምንጭ ከተማም ወደወላይታ እንዲዞር ሞክራችሁ ነበር፣ የአዋሳ ከተማም ወደወላይታ እንዲዞር መክራችሁ ነበር። እንደእውነቱ ከሆነ አርባምንጭ የደቡብ ዋና ከተማ መሆን አይገባትም ነበር? በነሺፈራውና በነሃ/ማሪያም ደሳለኝ ሴራ ይሄው አርባምንጭ አንድም ድንጋይ ሳይፈነቀልባት እንደው ባዶ ኦና ሆና ትኖራለች። ወላይታ ሶዶ ግን እነደመቀሌ ከባዶ ሜዳነት በአጭር ጊዜ ውስጥ ትንሿ አዲስ አበባ እንደሚትሆን ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ ቃል እየገቡላት ነው። እንግዲህ ልዩነት ሳይኖረን ልየነት እየፈጠራችሁ፣ ከህዝብ በወያኔ ፍርደገምድልነት ባገኛችሁት ስልጣን ተጠቅማችሁ ለጥቅማችሁ ስትሉ ይሄው ህዝባችንን በትግራይ ቅኝ ግዛት ስር ጣላችሁን። እንግዲህ ሳንወድ የግድ ዘረኞች ልታደርጉን ስለሆነ ትንሽ ጠንቀቅ ብትሉ እንላለን። ልማቱም ይሁን እደገቱ ለሁላችን እኩል የማይታደል ከሆነ መሬታችንን ለቀቁ፣ ባህላችንን መልሱ፣ ድንበራችንን አክብሩ፣ እናንተንም ወደአገራችሁ ግቡ ወደማለት የግድ እናመራለን።

ከትግራይ ዘረኛ መንግሥት ጭቆና የተነሳ የአማራና የኦሮም ብሎም የብሔር በሄረሰቦች መጨረሻ የሌለው የርስ በርስ የጦርነት ድባብ
የኢትዮጲያ መንግሥት ከሙስና ነጻ መውጣትና መልካም አስተዳደርን ማስፈን ለኢትዮጲያ መረጋጋት መፍትሔ ነው ብሎ ቢያምንም ቁልፍ የሆነውን የዲሞክራሲ ጥያቄ ከግምት አላስገባውም። በኢትዮጲያ ውስጥ ዲሞኪራሲ መምጣት ካልተቻለ በአገሪቱ በፍጹም ሰላም ሊመጣ አይችልም። ይህን በምንልበት ወቅት ባደጉትም አገሮች በአሜሪካ ዶናልድ ትርምፕና ኬኬኬ፣ በእንግሊዝ ጆንሰን፣ አረብ አገሮች አይ ሲ ሲ፣ በኤርትራ የኢሳይያስ መንግስት፣ በኮሪያ የኪም መንግሥት፣ በራሺያ የፑትን መንግስት ለአለም ሰላምና መረጋጋት እጅ አስፈሪ የመሆኑን ያህል በኢትዮጲያም ኢሃደግ፣ የኦነግ አክራሪ ብድንና ሞረሽ ወጌነ የአማራ አክራሪ ቡድን አገሪቱን እጅግ በሚያስፈራ ስጋት ላይ ጥለው እናገኛለን። በኢትዮጲያ የዲሞኪራሲ ያለመኖር ችግር አገሪቱ ወደማትወጣበት ችግር እንዲታመራ መሆኑን ሁሉም ቢያውቅም ኢሃደግ በጠመንጃ ሌላው ደግም በቅም በቀል ጠብቀኝ ላይ ሆነው ኢትዮጲያ ወደማትወጣበት የርስ በርስ መተላለቅ ብዙም ሳይቆይ እንደምትገባ ምልክቶች አሉ። ኢትይጲያ የምትፈልገው መታደስ ሳይሆን መሰረታዊ የፖለቲካ ለውጥ ነው፣ ስላዚህ ልብ ያለው ልብ ይበል። አገሪቷ ተዘርፋ ባዶ እየቀረች ዝም ብሎ የሚያይ ዘጋ ብቻ ከበዛ እዳው የመጪው ትውልድ ነውና ወጣቱ አይኑን ከፍቶ ማየት አለበት ባይ ነኝ።

     Give your opinion.