የጋም ጎፋ ካብነት ሽግሽግ በአምባ ገነን ወያኔ መንግስት፣ ከጋሞ ጎፋ ዜና አገልግሎት የተወሰደ

1-5-2017

ጋሞ ጎፋ የሚባለው ክ/ሃገር አንድ ህዝብ፣ ጎሳ፣ ዘር፣ ወግ፣ ባህል፣ ስራዓት፣ ቋንቋ፣ እና ወዘተ ያለው ህዝብ ቢሆንም በዝርዝር ዘገባው ውስጥ እንደተቀመጠው የጋሞ እና የጎፋ ጎሳ በሚል በመለያየት ካቢነውን አስቀምጠውታል። ይህ እውነት አይደለም። እኛ አንድ ነን። ጎፋ የሚባል ህዝብ የለም ጋሞ ጎፋ እንጂ። መረጃው ከአፄ ሚንሊክ ጦርነት በፊት አንድ ህዝብ እንደሆንን ይናገራል። ነፍጠኞች ከገቡባት ቀን ጀምሮ የተለያየ ዜጋ ለማድረግና ለመለያት እንደጣሩ፣ ማዶላዊያን ባገኙት በዚህ ክፍተት አማካኝነት ልዩ ህዝብ ለማድረግ ሞክረዋል። አልፎ ተርፎ ሰድበውናል። ቁም ነገሩ የጎፋ ህዝብ አጥንቱንና የአፈጣጠር መስመሩን (posture) መቀየር አለመቻላቸው እንጂ፤ ቢችሉ ኖሮ በሰሩት ሙቪና በመሳሰሉት መረጃዎች አማካኝነት ጋሞ ጋፋ አትኖርም ነበር። ታርክም አይኖራትም ነበር። ነገር ግን መገንዘብ ያልቻሉት እኛ እውነተኛ የጋሞ ጎፋ ተወላጆች እያለን ጋሞ ጋፋ ልትጠፋ ቀርቶ የበለጠውን ጎልተንና በልጠን ለመጪውም ትውልድ እውነተኛ ታርክ ዘግበንና አስተላልፈን እንደምናልፍ አልገባቸውም። ይህ የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ ነው። ጎፋ የሚል ዘር አለ በሚሉ የዘመኑ ባለስልጣናት አማካኝነት ጎፋና ጋሞ በሚል ሲከፋፍሉን አብጠርጥሮ ማየት ያቃጣቸውን የዘመኑን ባለስልጣናት የታርክ ጉድለት አለባችሁ እንላለን። ጎፋን ለመለየት ሲሉ የተለየ ጥብቆም አልብሰዋቸዋል። ቀበልኛን እንደቋንቋም አድርገው ለመቁጠር ሞክረዋል። የኦሞትክ ህዝብ ማናቸውም ቢሆኑ የቋንቋ መግባባት እንዳላቸ ቢገባቸውም ጎፋን ለመለት ሲሉ አንድ መሆናችንን እንዲንጠራጠር ድረስ አድረገዋል። ታዲያ ታርኩን ጥብቆ ማልበስ ይችሉ ነበር ወይ? በፍጹም! ለነፍጠኞችና ለዚህ ለታሪክ ወድቀት ላመሩን ሁሉ ጊዜ ይፈጃል እንጂ ታርኩ የኛ እንጂ የማንም አይደለም። ስለዚህ ብዙ ታርክ ገና የሚሰሩ ምሁራንን እያፈራን ስለሆነ ግና ብዙ ታርክ እንሰራለን ባይ ነኝ። የጻፋችሁትን የሃሰት ታርክ እንደገና ከልሰን እንጽፋለን። ከለያያችሁንና ታርክ ያለ እንጂ የተፈጠረ ባለመሆኑ በሚለያዩን ላይ ጥያቄ ምልክት ሁሌም ያተኩራል እናላለን። www.southernethiopiaonline.com

የጋሞ ጎፋ ዞን ነባርና አዳዲስ አመራሮች ሹመት ይፋ ሆነ
ድርጅቱ በታሪካዊ ጥልቅ ተሃድሶው ባወጣው ዝርዝር የግምገማ ነጥቦች በአመለካከት ፣ከብልሹ አሰራር፣ ሙስናና ኪራይ ሰብሳቢነት፣ ከአመራር ውጤታማነትና ከውስጠ ድርጅት ትግል ፣ ከመልካም አስተዳደር ፣ ከስነ-ምግባር እና ትርፍ መሬትና ቤት በሚሉ ዝርዝር ነጥቦች የዞኑ ማዕከል አመራር እንደዚሁም የ17 መዋቅር አመራሮች ተገምግመው እንዲያልፉ ተደርጓል፡፡
በዚህ መሰረት በዞኑ ካሉ 54 ዋና እና ምክትል አመራሮች መካከል 8 ወንድና 2 ሴት አመራሮች ከኃላፊነት ተነስተዋል፡፡ በመልሶ ማደራጀትም 6 ወንድ እና አንድ ሴት በድምሩ 7 አመራሮች እንዲነሱ ተደርጓል፡፡ ደግሞ 26 ወንድ እና 6 ሴት በድምሩ 32 በአመራሪነት እንዲቀጥሉ የተደረጉ ሲሆን 19 ወንድና 2 ሴት በድምሩ 21 አዳዲስ አመራሮች ፑሉን ተቀላቅለዋል፡፡
የጋሞ ጎፋ ዞን ሕዝብ ምክር ቤት ሰሞኑን ባካሄደው 4ኛ ዙር መረሃ ግብር 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን አንደኛ አስቸኳይ ጉባኤ በትምህርት ደረጃቸው ፣ በአመራር ውጤታማነት የፖለቲካ ብቃት እና የሙያ መስመርን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የዞኑን ነባር እና አዳዲስ አመራሮች ሹመት አጽድቋል፡፡
በዚህ መሰረት፡-
ባሉበት እንዲቀጥሉ የተደረጉ ነባር አመራሮች
1. የተከበሩ አቶ ኢሳያስ እንድርያስ
ብሔረሰብ ፡- ጋሞ
የትምህርት ደረጃ፡- በህዝብ አስተዳደርና ልማት አመራር የመጀመሪያ ድግሪ
የተመደቡበት የስራ ኃላፊነት፡- የጋሞ ጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ

2. የተከበሩ አቶ ተፈሪ አባተ
ብሔረሰብ፡- ጎፋ
የትምህርት ደረጃ፡- በአካውንቲንግ የመጀመሪያ ድግሪ
የተመደቡበት የስራ ኃላፊነት፡- የጋሞ ጎፋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የዞኑ ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ኃላፊ
3. አቶ ቱርቃቶ ቱርቶ
ብሔረሰብ፡- ጎፋ
የትምህርት ደረጃ፡- በአመራር ሳይንስና መልካም አስተዳደር የማስትሬት ድግሪ
የተመደቡበት የስራ ኃላፊነት፡- የጋሞ ጎፋ ዞን ደኢህዴን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ

4. አቶ አይሶጼ ሂሎታ
ብሔረሰብ ፡- ጋሞ
የትምህርት ደረጃ፡- በኢኮኖሚክስ የመጀመሪያ ድግሪ
የተመደቡበት የስራ ኃላፊነት፡- በጋሞ ጎፋ ዞን ደኢህዴን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ
5. አቶ ሐኪሜ አየለ
ብሔረሰብ ፡- ጋሞ
የትምህርት ደረጃ፡- በስታስቲክስ የመጀመሪያ ድግሪ
የተመደቡበት የስራ ኃላፊነት፡- በጋሞ ጎፋ ዞን ደኢህዴን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የከተማ ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ

6. አቶ አሸብር ደምሴ
ብሔረሰብ ፡- ጋሞ
የትምህርት ደረጃ፡- በገጠር ልማትና ስነ-ምግብ ሳይንስ የመጀመሪያ ድግሪ
የተመደቡበት የስራ ኃላፊነት፡- የጋሞ ጎፋ ዞን እርሻና ተፈጥሮ ሐብት መምሪያ ኃላፊ

7. ኢንጂነር አድማሱ ባላ
ብሔረሰብ ፡- ጎፋ
የትምህርት ደረጃ፡- በሲቪል ኢንጂነሪንግ የመጀመሪያ ድግሪ
የተመደቡበት የስራ ኃላፊነት፡- የጋሞ ጎፋ ዞን ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ

8. ዶክተር አፈወርቅ ከተማ
ብሔረሰብ፡- ጋሞ
የትምህርት ደረጃ፡- 12+6 በእንስሳት ሕክምና
የተመደቡበት የስራ ኃላፊነት፡- የጋሞ ጎፋ ዞን እንስሳትና አሳ ሐብት መምሪያ ኃላፊ

9. አቶ ሽመልስ ታደሰ

ብሔረሰብ ፡- ጋሞ
የትምህርት ደረጃ፡- በኢኮኖሚክስ የመጀመሪያ ድግሪ
የተመደቡበት የስራ ኃላፊነት፡- የጋሞ ጎፋ ዞን ንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ ኃላፊ

10. አቶ ማሔ ቦዳ

ብሔረሰብ ፡- ጋሞ
የትምህርት ደረጃ፡- የመጀመሪያ ድግሪ በኢኮኖሚክስና የማስትሬት ድግሪ በአመራር ሳይንስና መልካም አስተዳደር
የተመደቡበት የስራ ኃላፊነት፡-የጋሞ ጎፋ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ

አዲስ የተሸሙ አመራሮች

1 . አቶ ቤታ አንጁሎ
ብሔረሰብ ፡- ጋሞ
የትምህርት ደረጃ፡- በህግ የመጀመሪያ ድግሪ
የተመደቡበት የስራ ኃላፊነት፡- የጋሞ ጎፋ ዞን ፀጥታ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ

2. አቶ ታምራት ተሰማ

ብሔረሰብ ፡- ጎፋ
የትምህርት ደረጃ፡- በዴቨሎፕመንታል ማኔጅመንት የማስትሬት ድግሪ
የተመደቡበት የስራ ኃላፊነት፡- የጋሞ ጎፋ ዞን ከተማ ልማት መምሪያ ኃላፊ
3. አቶ ተሻለ ማናዬ
ብሔረሰብ ፡- ጋሞ
የትምህርት ደረጃ፡- MPh in Nutrition
የተመደቡበት የስራ ኃላፊነት፡-የጋሞ ጎፋ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ

4. አቶ ጌትነት ስንታየሁ

ብሔረሰብ ፡- ጎፋ
የትምህርት ደረጃ፡- በህግ የመጀመሪያ ድግሪ
የተመደቡበት የስራ ኃላፊነት፡-የጋሞ ጎፋ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ

5. ወ/ሪት ፀጋነሽ እንግዳ

ብሔረሰብ ፡- ጎፋ
የትምህርት ደረጃ፡- የማስትሬት ድግሪ በማቲማቲክስ
የተመደቡበት የስራ ኃላፊነት፡- የጋሞ ጎፋ ዞን ሴቶችና ህጻናት መምሪያ ኃላፊ

6. አቶ ካምቦ ዴሮ

ብሔረሰብ ፡- ጋሞ
የትምህርት ደረጃ፡- በቱሪዝም ማኔጅመንት የመጀመሪያ ድግሪ
የተመደቡበት የስራ ኃላፊነት፡- የጋሞ ጎፋ ዞን ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚዩንኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ

7. ወ/ሮ ልሳነወርቅ ካሳዬ

ብሔረሰብ ፡- ጋሞ
የትምህርት ደረጃ፡- በህዝብ አስተዳርና ልማት ስራ አመራር የመጀመሪያ ድግሪ
የተመደቡበት የስራ ኃላፊነት፡- የጋሞ ጎፋ ዞን ዋና አፈ-ጉባኤ

8. አቶ ዳበሮ ዳልጮ

ብሔረሰብ ፡- ጋሞ
የትምህርት ደረጃ፡- በልማት ስራ አመራር የማስትሬት ድግሪ
የተመደቡበት የስራ ኃላፊነት፡- የጋሞ ጎፋ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት መምሪያ ኃላፊ

9. ኢንጂነር ተስፋሁን ጉሌ

ብሔረሰብ ፡- ጎፋ
የትምህርት ደረጃ፡- በአርባን ኢንጂነሪንግ የመጀመሪያ ድግሪ ፣ በኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ ማናጅመንት የመጀመሪያ ድግሪ እና በሲቪል አንጅነሪንግ የማስትሬት ድግሪ
የተመደቡበት የስራ ኃላፊነት፡- የጋሞ ጎፋ ዞን መንገድና ትራንስፖርት መምሪያ ኃላፊ

10. ኢንጂነር መኮንን ንጋቱ

ብሔረሰብ ፡- ጋሞ
የትምህርት ደረጃ፡- በሲቪል አንጅነሪንግ የማስትሬት ድግሪ
የተመደቡበት የስራ ኃላፊነት፡- የጋሞ ጎፋ ዞን ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ

11. አቶ አሸናፊ ናና

ብሔረሰብ ፡- ጋሞ
የትምህርት ደረጃ፡- በአካውንቲንግና ፋይናንስ የማስትሬት ድግሪ
የተመደቡበት የስራ ኃላፊነት፡- የጋሞ ጎፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ

12. ወ/ሮ መሠረት አየነው
ብሔረሰብ ፡- ጋሞ
የትምህርት ደረጃ፡- የማስትሬት ድግሪ በሕዝብ ፖሊሲ ጥናት
የተመደቡበት የስራ ኃላፊነት፡- የጋሞ ጎፋ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ

     Give your opinion.