ጋሞኦ ደሬ ወይም ጋሮ ማለት ምንድነው? በእውነትም ጎፋ የተባለ አገር ወይም ዘር ነበር ወይ?

1-31-2017

ጋሞኦ ደሬ ወይም ጋሮ ማለት ምንድነው? በእውነትም ጎፋ የተባለ አገር ወይም ዘር ነበር ወይ?
በአፄ ሚኒሊክ ወረራ ወቅት በቦረና፣ በኮንሶ፣ በጸማይ፣ በጂንካና በኡባማሌ አድርጎ ወደመጣበት የሚመለሰው የጂማው አባ ጅፋር ጦር (በሚኒሊክ ሥር) አብዛኛው በጂንካ፣ በጋዘር፣ በኡባ ደብረጸሃይ፣ በቡልቂ፣ በመስከቶ፣ በሳውላ (ፈለገንዋይ) ሰፍረው እንደቀሩና አካባቢውንም እንደተቆጣጠሩ የጎፋን አውራጃንም ጎፋ(አስለቅቀን የያዝነው የኛው ንብረት) ብለው እንደሰየሙ የጂንካው ግራዝማች ከበደ ካሣ ይናገራሉ። ጎፋ ማለት በአማሪኛው ነጠቀ፣ አስለቀቀ ማለት ነዉ። ጎፋ አካባቢ ያሉትን ከተሞች ደብረፀሃይን፣ ቡልቂን፣ ቀይአፈርን፣ ሳውላ ፈለገነዋይን፣ ቱካ (ጨንቻ)፣ የጋንታ አገር የነበርውን መሬት አርባምንጭ በማለት፣ ዱዳኔ የሚባለውን ምዕራብ አባያ፣ ቆላ ኦቾሎን ላንተ፣ ኦሮሞን ጋላ፣ ወላይታውን ወላሞ፣ ሃዲያውን ጉደላ፣ ጋሞዖኦውን ገሙ በርካታ የስድብና የማዋረጃ ሰም ጭምር ሰጥተው በአማሪኛ ሰይመዋል። እነዚህን ሁሉ ስንመለከት ከአማሪኛና አልፎ አልፎም ከኦሮምኛ የተወረሱ ስሞች ናቸው። በደቡብ ቦረና በኩል የመጡት እነዚህ ወታደሮቹ የኦሮሚኛ ተናጋሪ ሲሆኑ፣ በሰሜን ምሥራቅ በኩል የወላይታውን ንጉስ ጦናንና የቦረዳውን ንጉስ ሜጋሮን በምስሌነ ድጋፍ ያሸነፈው የሚኒልክ ወታደሮችና ቀሳውስቶች የአማራ ብሔርሰብ በመሆናቸው ባልፉባቸው አከባቢ ያለውን ሕዝብ በአማሪኛም ሆነ በኦሮምኛ ቋንቋ እንዲናገሩ ተጽዕኖ አድርገዋል። ከዚህም የተነሳ ነበር የጂንካ አሪ ህብረተሰብ ሰላምታውንና ሃዘነታውን አቦ ብለው የቀሩት ሲሉ እኚህ አዛውንት ግራዝማች ከበደ ካሣ በዶ/ር ሳሙኤል ጎንደሬ በኩል ለጂንካ ት/ቤት መዝጊያ በተዘጋጀው እንተርቪው መጽሔታቸው ላይ ይናገራሉ። አዎ እውነትም ጂንካ ከተማ ውስጥ ሰላምታውና የሃዘን መግለጫው አንድ ቃል አቦ እንደሆነ ራሴ አይቸዋለሁ። አቦ ለሰላምታም ሆነ ለሃዘነታ አድርገው የወሰዱበት ዋናው ምክንያት እነዚህ የኦሮሞ አባ ጅፋር ወታደሮች (በሚኒሊክ ሥር) ጓደኞቻቸውን አቦ (ወንድሜ ወይም ጓዴ) ብለው ሲጠሩ የሰሙት የአካባቢው ህዝብ ሰላምታ መስሎአቸው እስካሁንም በዚያው ቀሩ ብለዋል።
ወታደራዊ ደርግ ስልጣን ሲይዝ እነዚህን መጥፎና የስድብ ስም ናቸው ብሎ ያሰቧችውን በሙሉ ለምሳሌ፡ -ጋላ የተባለውን ኦሮሞ፣ ወላሞ የተባለውን፣ ወላይታ፣ ጉደላ የተባለውን ከንባታና ሃዲያ፣ አሩሲ የተባለውን አርሲ፣ ገሙ የተባለውን ጋሞ፣ ሻንቅላ የተባለውን ጋምቤላ፣ ወዘተ.. .ሌሎችንም ህዳጣን በሔረሰብ የተባሉትን በሙሉ የስም ለውጥ በማድረግ አስተካከሉ። ጋሞኦ እንደአንበሳ የተተረጎመው ከደርግ ወዲህ ነው። ቅድሜ ስሙ ጋሞኦ ነው። በርግጥም አንበሳ ሊሆን ይችላል።
እዚህ ላይ ለየት አድርጌን ማየት ያለብን ነጥብ ጋሞ የሚለው ስም ነው። አቶ ታዳላ ቱፋ (ከጂማውአባ ጅፋር ሠራዊት ጋር ከመጡ ወታደሮች የአንዱ ልጅ) ሲሆን የጻፈው መጽሃፍና ግኝት ነው ብሎ በጋሞ ጎፋ ሕዝብ ውስጥ የጫረው እሳት መነሻም ሆነ መድረሻ የሌለው ሆኖ አባቱና ጓደኞቻቸው የተፈላሰፉት የእብሪትና የቅኝ ገዥነት የተንኮል ተልዕኮ ነጸብራቅ ነው። ተንኮላቸው ጎፋን ጎፋ ብለው ከሰየሙ በኋላ ይህ ስም ከጥንት ጀምሮ ያለና የነበረ አስመስለው እነርሱ ስም ስላወጡ ብቻ ብለው የሰራነው የተንኮል ታርካችን ከሚጠፋ እንዳለ ደቡብን እርስ በርስ አጋጭተን ማጥፋት ነው ብለው የጠነሰሱት የተንኮል ውጤት ነው። ማዶላ የሃሰት ፍልስፍና ስለሆነ አሁንም ቢሆን ያልተጻፈና ያልነበረ ከጊዜ በኋላ ተቆርጦ የተቀጠለ ታሪክ ስለሆነ ይጠፋል። አንድ ህብረተሰብ ይወለዳል ያድጋል ይከስማል በሚል አስተሳሰብ ተመስርቶ እኛ የምንሰራውን ሥራ ማንም አይውቀውም ብለው የፈጠሩት ደባ ካልሆነ በስተቀር የዳሞት ኢናሪያ ወይም የኦሞትክ ህዝቦች ወይም የጋሮ አገር እኛ ልጆቿ እያለን በዚህ ተራ ፍልስፍና ሊጠፋ አይችልም።
በተለይ መርጃዎቹን እንደመረጃ አምነን የምንቀበለው ኢትዮጲያ በአዲሱ በዘረኝነት አዝመራ ላይ መሠረት አድርገው እያንዳንዱ ስለራሱ ጭቃሹምነት እየሰበከና እያደላ የጻፈውን፡(ከ1990ቹ ወዲህ) ያለውን ሳይሆን በተለይ ከዚያ ቀድመው ብለው በተጻፉት ላይ 70% እምነት ብንጥል መልካም ነው። ሁሉም የዩንቬርሲቲ ተመራማሪዎች ይሳሳታሉ ለማለት ሳይሆን ከቀድሞውም ሆነ ካአሁኑ የሚቀሩ ብዙ መርጃዎች ስላሉ ነው። ስለሃላላ ኬላ(ዳውሮ) የተጻፈው ምርምርና መረጃ አሰባሰብ ተጨባጭና እንከን የማይወጣለት ነው። እነጆሹዋ ፕሮጀክት የመሳሰሉትን እንደመረጃ መውሰድ ደግሞ ብቃት ወዳለው መሳሳት ይወስደናል።
ጋሞ ማለት በመሰረቱ አንበሳ ሊባል ታስቦ የተሰጠ ስም ሳይሆን የጥንት የቅማንት ስሙ ራሱ ጋሞኦ (ጋሮ ወይም ታላቅ የማምለኪያ ቦታ) ማለት ነው። አጠራሩ ሁለት ነው። ጋሞ አንበሳ ሲሆን ጋሞኦ ማለት የጋሞኦ ሕዝብ መጠሪያ ጥንተ ስሙ ነው። በታሪክ እንደምናየውም ሆነ በቅድሜ አያቶቻችን እንደተነገረው ወይም እንደሚታወቀው ጋሞኦ እንደሚከተለው ተቀምጦአል።
በሃበር ላንድ ጆርናል እንደተቀመጠው ከክቡር አቶ ተስፋዬ ሃቢሶ ጽሁፍ በተወሰደው እንዲህ ይላል። “Besides, many ruling dynasties of southern Ethiopian states claimed Amhara or Tigray descent: Kaffa, Kambata, Wolayta, Zay, Amarro-Koyra, Janjero [Yem], Dorze, Gamo, Bosha, Gurage, etc”. {Haberland, Journal of Semitic Studies, Vol. 9, No. 1, የአማራና የትግሬ ቅኝ ገዢዎች ሲቀሩ ተበድለውና ተጎሳቁለው የኖሩ የደቡብ ሕዝቦችን እንደሚከተለው ያስቀምጣል። ከፋ፣ ካምባታ፣ ወላይታ፣ ዘይ፣ አማሮ፣ ኮይራ፣ ጃንጀሮ(የም)፣ ዶርዜ፣ ጋሞ፣ ቦሻ፣ ጉራጌ ብሎ ይዘረዝራል።
ሌላው ደግሞ ጥናት እንደሚያመለክተው “ in the 13th and 14th centuries, these peoples were part and parcel of the State of Damot- Ennariya that also included other peoples such as Damot, Ganz, Gafat, Kaffa, Kullo, Konta, Wolayta, Maraqo, Yem, Garo, Azernete-Berbere and Enner Gurage(Ennariya). Damot- Ennariya, including Kambata and many others for over four hundred solid years.” ጥናቱ እንደሚያመለክተው ከዚህ በታች ያሉት በሄረሰቦች በአንድ ዳሞት እናሪያ አስተዳደር ስር ለ400 አመታት ይገዙ ነበር ይላል። እነዚህም ዳሞት፣ ጋንዝ፣ ጋፋት፣ ካፋ፣ ኩሎ፣ ኮንታ፣ ወላይታ፣ ማራቆ፣ የም፣ ጋሮ፣ አዘርነት፣ እና ሰባት ጉራጌ ይላል።
ሌላው ጥናት ደግሞ “Fitawrari Bargano Mollisso (1920-47) in the following words:“--- Whence came all these people? They came from the lands of the Amhara, the Galla [Oromo], the Sidama , the Darassa [Gedeo] , the Wolammo [Wolayta], the Gudela [Hadiya], the Gamo, the Zubamo [Dubamo], the Gurage, the Tembaro, the Donga, etc. They are a mixture of all these peoples---“ ፍታውራሪ በርጌኖ ሞሊሶ የገዙት(1920-1947) ሲሆን እነዚህ ሰዎች(ካምባታዎች ለማለት) ከየት መጡ ለሚለው ጥያቄ መልሱን እንዲህ ብለውል። እነዚህ ሰዎች የመጡት ከአማራ፣ ከኦሮሞ፣ ከሲዳማ ፣ ከደራሳ፣ ከወላይታ፣ ከሃዲያ፣ ከጋሞ፣ ከዱባሞ፣ ከጉራጌ፣ ከጣምባሮ፣ ከዶንጋ ወዘተ... ብለው ይደመድማሉ።
ሌላው ጥናት እንደሚያመለክተው “I could point out to you a family whose grandfather was an Ongota (of Amhara origin) whose wife was a Gabara (of Oromo origin) , whose son married a Doda- Annimanna (Badawacho Hadiya), and whose present four sons have now four wives of different clans claiming diverse origins—a Jumma (Sidama), a Wereza(Azernet- Berbere), a Bubulla (Wolayta) and a Borodamalla (Gamo) respectively. He is a Kambata, who, leaving behind him all his ancient prejudices, affiliations, roots and manners, receives new ones from the new mode of life he has embraced, the new government he obeys, and the new rank he holds” ስለ አንድ አማራ ኦንጋታ ሰለሚባል ሰው ልንገራችሁ።ምስቱ ከኦሮሞ ልጁ ያገባው ከሃዲያ፣ ከልጁ የተወለዱ አራቱም ልጆች ከተለያዩ ብሄረሰቦች አግብተዋል። አንዱ ከዎላይታ ቡቡላ ዘር፣ አንዱ ከቦረዳ ማላ (ጋሞኦ) ዘር፣ አንዱ ደግሞ ከሲዳማ ዘር፣ እና ሌላው አዘርነትና በርበር ዘር አግብቶ እርሱ ግን ከንባታ ሆኖ የሁሉንም እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ የሚለውን ሁሉ ተሸክሞ ለህግ እየታዘዘና እያስተዳደረ ዕድሜውን ይገፋ ነበር ይላል።
ሰለዘር አቆጣጠርና አመጣጥ ሲናይ። በጋሞ ደሬዎች በጠቃላይ ማለት በአርባሁለቱም፣ (ቆጎታ (ጨንቻና ኤዞ)፣ ውሳሞና ጻይቴ፣ አልጉዴ(ሜሌ)፣ ጋርባብሳ፣ ጮዬ፣ ዶኮ (በጎፋ ያለውን ጨምሮ)፣ ቁጫ፣ ድንጋሞ ኦቶሎ፣ ቦረዳ፣ ጋንታ፣ ቦንኬ፣ ማሎ፣ ሻማ፣ ኦቾሎ፣ ዛሜ፣ ጋጼ፣ ሸላ፣ ካምባ፣ ጋርዳ፣ ሻራ፣ ካምዓለ፣ አንኮ፣ ሃንቃ፣ ዛርጉላ፣ ዚጊቲ፣ ገረሰ፣ ማርታ፣ ባልታ፣ ሀርንጋ፣ ዶቃማ፣ ማናና፣ ወበራ፣ አንድሮ፣ ዛራ፣ ዲታ፣ ዳራ፣ ዶርዜ፣ ኤሊ፣ ጉጌና ኮዶ) እና በወላይታ፣ በከንባታ፣ በዳውሮ፣ በየም፣ በካፍቾ እያንዳንዱን ዋና የዘር ግንድና ንዑስ የዘር ክፍፍል ሲኖራቸው በታሪክም ሆነ በቅድሜ አያቶቻችን አፌ ታሪክ ከአጼ ሚኒሊክ አገዛዝ በፊት ጎፋ የሚባል አገርም ሆነ ዘር እንደሌለ ያረጋግጥልናል። ጎፋ ማላ የሚል ዘር፣ የጎፋ ቡቡላ፣ የጎፋ አርጋማ፣ የጎፋ ማካ፣ የጎፋ ህዚያ፣ የጎፋ ጉዳረታ ወዘተ የለም። በርካታ የጎፋ ኦርጅናል ተወላጆችን አግኝተን አነጋግረናል። 100% ታዳላ ቱፋ ዋሸ።
References
1. Atme, G.M. History of the Galla (Yegalla Tarik), part I translated by Bairu Tafla, O.O. (Ms) Azais, R. P.and R. Chambard , 1942.
2. Braukamper, Ulrich, Die Kambata Franz Steiner Verlagh GMBH, Weisbaden, 1983
3. Buckingham, C.F. and G. B.W. Huntingford (Eds.). Some Records of Ethiopia 1593-1646; Being Extracts from the History of High Ethiopia or Abassia by Manoel de Almeida together with Bahrey’s History of the Galla [Oromo ], (Hakluyt Society II, CVII), London
4. Cerulli, Ernesta Peoples of South –west Ethiopia and its Borderland, London, 1956
5. Ethiopia: The 1994 Population and Housing Census of Ethiopia, CSO, 1994, Addis Ababa
6. Haberland, E. The Influence of the Christian Ethiopian Empire on Southern Ethiopia , In Journal of Semitic Studies IX: 235-38
7. Hodson, A. Seven Years in Southern Ethiopia , London, 1927
8. Leslaw, W. Additional Notes on Kambata of Southern Ethiopia, In: Arthropods 51, 5/6 :985-93 , 1956
9. Leslaw, W. Notes on Kambata of Southern Ethiopia, In: Africa, XXII:348-59 , 1952
10. Ludolph(us), J. A New History of Ethiopia: Being a Full and Accurate Description of the Kingdom of Abyssinia, vulgarly though Erroneously called the Empire of Prester John, London, 1682.
11. Moreno, M.M. Appunti di Cambata e di Alaba, In: RRAL, ser. VI, XIV,3/4=269-79
12. Singer, N.J. The Use of Courts as a Key to Legal Development: an Analysis of Legal Attitudes of the Cambata of Ethiopia, In Proceedings of the First United States Conference of Ethiopian Studies, 1973. s. 365-83 East Lansing , 1975
13. Singer, N.J. Some Notes on the origin of the Cambata of southern Ethiopia, Tuscaloosa (Ms.), 1977.
14. Singer, N.J. The Relevance of Traditional Legal Systems to Modernization and Reform: a Consideration of Cambata Legal Structure, In Tubiana, J. (Ed.), Modern Ethiopia :From the Accession of Menelik II to the Present, S.. 537-56 ,Rotterdam , 1980
15. Yigezu, Seifu. Kambata Awraja: Its People and Local Administration, Addis Abeba (Ms)1970.
16. Dagana Bafutte Did’ana Oral History of Kambata, 1986. The late
Dagna Bafutte Did ‘ana was a well known Oyeta notable who died at the age of 90 in 1992.
Saturday, 14 July 2012

     Give your opinion.